የማሃሪ የውሀንሥ ሸንደፍደፍ ወዴት ምንለማግኜት  (ከትላንትና የቀጠለ) – አስገደ ገ/ ስላሴ

ሁሉ ያንብበው

የማሃሪ የውሀንሥ ሸንደፍደፍ ወዴት ምንለማግኜት

ከትላንትና የቀጠለ
mekelle-university-ayder-1የሀወሓት ሎሌና የውሸት ማሥተላለፍያ ጋተር የሆነው መሃሪ የውሃንሥ ሥለወልቃይት ጸገዴ አርማጨሆ የማንነት ጥያቄ በሚመለከት ያሥቀመጠው ትንታኔ የፓለቲካዊ ሣይንሥ ሙሁር ትንታኔ ሣይሆን  እጅጉን የወረደ ኋላ ቀር መሥፍናዊ ኣገላለጽ ከመሆኑም በላይ ለመቀሌዩነቨርሲቲ ሊሂቃኖች ያዋረደ መሆኑ ነው የሚያሣዝነው
ሥለወልቃይት ጸገዴ ከተነሣ  ኣሁን ተፈጥሮ ያለ ሠጣገባ የህወሃት ኢህኣደግ በቋንቋና በባህል የመካለል ፈደራሊዝም
የፈጠረው ጠንቅ መሆኑ ሁሉም በዲሞክራሲ እና የሠባኣዊ
መብት ኣጠባበቅ  ትርጉም  የሚረዱ ህዝቦች ይረዱታል
ለመሃሪ የውሃንሥ  እና ጌቶቹ ግን ሠሚጀሮ ካላቸው  ሃቁን እነግራቸው ኣለሁ  ::
በወልቃይት ጸገዴ ይሁን በሌሎች ክልሎች ያለው የኣከላለል ጥያቄ መሆን የነበረበትና ያለበት የከላለል   ህግ ከዚህ በታች ያሉ  ሞሟላት ኣለባቸው::
የህዝቡ ታሪካዊ ኣመጣጥ: የህዝቡ ጂኦግራፊያዊ ኣቀማመጥ:  የህዝብ ባህል ና ልምድ: የህዝቡ ኣሥተሣሠብ ወይ ሣይኮለጅካል ሜክኣብ : ቃንቋና ባህል:የኣሥተዳደር ሙችውነት: ማካተት ኣለበት:  :
በመሃሪ የውሃነሥና ጌቶቹ ግን ይህ ሃቅ  ተከትለው ሠጣገባውን እንደመፍታት ያየ1968 ዓ ም  ጠባብነት ተጧናውቶባቸው  የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የህወሓት ካድሬዎች  በኣበይወልዱ  እየተመሩ  በሠለማዊ ሠልፍ በኮንፍረንሥ በሠሚናር እየናጡ የጦርነት ሞዝሙር በማዘመር  ወደጦርነት ጎዳና እንዲዘምት እያረጉ ይገኛሉ::
በሌላ በኩል በኣማራ ክል  በገድሉ ኣንዳርጋቸው እና ቅጥረኛ ካድሬዎቹ ለጎንደር ህዝብ ባልሆነ መንገድ በዘረኝነት እየናጡ ወደጦርነት ኣውድማ እየጋበዙት  ይገኛሉ:: የሁለቱን ፓርቲዎች ጦሥ ወደ ህዝብ ወርዶ  እሣት እንዲቀጣጠል ከርቢትን በማቀበል  ደግሞ የኣርባዕተ ኣሥመራ ተወላጅ   የሆነው እንደ መሃሪ የውሃን  ያሉ በሥመሙሁራን ኣድርባይ ውሼት በመርጨት  ይሯሯጧሉ  ይህ  ግጭት በወልቃይት ጸገዴ  እና በኦሮሞ ታጥሮ የሚቀር ኣይደለም :: በራያ ቆቦና  በወሎም ጥያቄ ከተነሣ ረጅም ጊዜ ያሥቆጠረ ቢሆንም  ኣሁን እንዳገረሸበትም ይናፈሣል ::
የዚህ ኣደጋ ከወዲሁ ለማርገብ ከተፈለገ የሃገራችን ሙሁራን እና የመላው ህባችን   ሓላፍን ቢሆንም   በተለይ ግን   እንደ መሃሪ የውሃንሥ  ድንጋይ ዳቦ ነበር  የሚሉ ሣይሆን በቁ የፖለቲካ ሣይንሥ  : የህግ ሙሁራኖች ወዘተ በጥንቃቀ  ተመልክተው   ሓቀኛ መፍትሄ ቢያፈላልጉ ተነሳሽነት ቢደርጉ  ያሻል ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.