አዲስ አበባ በታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ተመታች

1

( ሳተናው) ትራፊክ ፖሊሶች በፌደራሎች እየታገዙ ታርጋ መገንጠል ጀምረዋል :: የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ጥፋት በሚፈጽሙና አደጋ በሚያደርሱ አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ለመጣል ያስችላል ያለውን መመሪያ ማውጣቱን ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ በማለት የተቃወሙት የአዲስ አበባ የታክሲ አሸከርካሪዎችና ባለንብረቶች ዛሬ ማለዳ ጀምረው የጠሩትን የስራ ማቆም አድማ በተግባር አውለውታል፡፡
በስራ ማቆም አድማው ምክንያትም የሸገር ነዋሪዎች ወደ ስራ፣ትምህርት aysuzuቤትና ወደተለያዩ ጉዳዩቻቸው ለመጓጓዝ ተቸግረው ተስተውለዋል፡፡በስራ ማቆም አድማው ምክንያት የተፈጠረውን ችግር ለመሙላት ሲሉም ፌደራል ፖሊሶችና ትራፊኮች የግል ተሸከርካሪዎችንና የጭነት መኪኖችን በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭኑ ሲያደርጉ ተስተውለዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሁሉም አቅጣጫዎች ታክሲዎች ሙሉ ለሙሉ በማለት በሚቻል መሉኩ በስራ ማቆም አድማው የተሳተፉ ሲሆን በመገናኛ ሲኤም ሲ፣ጉርድ ሾላና አውቶብስ ተራ አካባቢዎች የደህንነት ኃይሎችና ትራፊኮች በፌደራል ፖሊሶች በመታገዝ የቆሙ ታክሲዎችን ታርጋ በመፍታት መውሰዳቸው ታውቋል፡፡
በትናንትናው ምሽት የትራንስፖርት ባለስልጣን አዲሱን የቅጣት መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ጊዜ ለሶስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉን መግለጹ አይዘነጋም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.