ከወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልቃይት ምድርና አካባቢው የሰፈነው ውጥረት አይሎ ሊፈነዳ ተቃርቧል

welkeit 4573ህወሓት ደጋፊዎቹን ከትግራይ በማጓጓዝ የወልቃይት ህዝብ የማንነቱን ጥያቄ ተቃውሞ አደባባይ የወጣ በማስመሰል የውሸት ሰላማዊ ሰልፎች እያደረገ ነው፡፡ ከሰሞኑ በጠገዴ ወረዳ ከተካሄደው የሀሰት የድጋፍ ሰልፍ በተጨማሪ ህወሓት 16 አውቶብስ ሙሉ ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በጠለምት፣ ደጀና፣ አደባይ እና በሌሎችም ቦታወች የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የሚቃወሙ ሰልፎች አካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሽፍቶች ቡድን ህወሓት በወልቃይት ህዝብ ላይ የሚያደርገውን እስር፣ አፈና እና ማዋከብ በእጅጉ አበርትቶታል፡፡ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄውን ህወሓት እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ይፈቱልኛል ብሎ የመረጣቸው ወኪሎቹ እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው፡፡ ህዝቡን ያስተባብራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የወልቃይት ወጣቶችም በየቀኑ እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ህወሓት ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ህዝብ ስም “እኛ ትግሬዎች ነን አማራዎች አይደለንም” በማሰኘቱ የወልቃይት ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ውስጡ እንደሻከረ እየተነገረ ነው፡፡

በመሆኑም በወልቃይት ሰማይ ስር ሊፈነዳ ከጫፍ የደረሰ የአመፅና የቁጣ ድባብ እያንዣበበ ነው፡፡
‪#‎ምንጭ‬ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.