ግብጽ 100.000 ተማሪዎቿን ለትምህርት ጃፓን ልትልክ ነው

sisi

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ለጉብኝት ወደ ጃፓን ቶኪዩ ከማቅናታቸው አስቀድሞ ጉዟቸውን በማስመልከት ለአገራቸው ጋዜጠኞች ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል፡፡
በቃለ ምልልሱ ስለ አህጉሪቱ ቀውሶች፣የትብብሮችን አስፈላጊነት፣በሊቢያ ያለው ሁኔታ ሽብርተኞች አገሪቱን እንደ ዋነኛ መንቀሳቀሻ ሊጠቀሙባት ስለመቻላቸውና በሌሎች ጉዳዩች ዙሪያ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡
ሲሲ ትናንት እሁድ ወደ ጃፓን ካመሩ በኋላም ለታዋቂው የቶኪዩ ጋዜጣ አሻሂ ሺምበርን ‹‹ከጃፓን ጋር ባለን ግኑኝነት ግብጽ ተጠቃሚ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡በተለይም የቶኪዩ ትምህርት ዘዬ ስነ ምግባርን አጽንኦት በመስጠት የሚካሄድ በመሆኑም ተማሪዎቻችን እንዲያልፉበት እንፈልጋለን››ብለዋል፡፡
ሲሲ 100.000 ግብጻውያን ተማሪዎችን ወደ ቶኪዩ መላክና የተሻለ ትምህርት ማግኘት የሚችሉበትን ዕድል መፍጠር እንደሚፈልጉም መናገራቸው ለንባብ በቅቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.