ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈቅዶ የነበረው ጥየቃ በድጋሚ ተከለከለ

Temesgen Desalegn behindbarየካቲት 20/2008 ከወደ ዝዋይ-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ -ውብሸት ታዬ ጨምሮ በዝዋይ የሚገኙ የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ዝዋይ ማረሚያ ቤት በጠዋቱ ቢደርሱም ትንታጉ ብዕረኛ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ- እሱን መጠየቅ አይፈቀድም በማለት ተከለከሉ፡፡ ከተመስገን ውጪ ያሉትን የህሊና እስረኞች በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በህመም እየተሰቃየ በወዳጅ ዘመን አድናቂዎቹ እንዳይጎበኝ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በድብቁ የህውሓት ማፊያ ቡድን የክልከላ ወንጀል እየተፈጸመበት እንደሚገኝ ከወደ ዝዋይ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ክብር ለህሊና እስረኞቻችን ነገም ዛሬ መናገራችን አናቆምም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.