ኦህዴድ በከር ሻሌ ለጽ/ቤቱ ቢመደቡለትም ዳባ ደበሌ የደረሱበት አልታወቀም

bkre

( ሳተናው ) የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በሚኒስትር ማዕረግ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ በከር ሻሌ የኦህዴድ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡በከር ለኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን እንዲሰሩ መመደባቸውን የሚገልጸውን ደብዳቤ ባሳለፍነው ሳምንት እንደደረሳቸው የጠቆሙ ምንጮች በያዝነው ወር በይፋ ቢሮውን ተረክበው መስራት ይጀምራሉ ብለዋል፡፡በከር የሚረከቡት የኦህዴድ ዋና ቢሮም የሚገኘው መስቀል አደባባይ የኦሮሚያ ባህል ማዕከል አጠገብ ነው፡፡
ከበከር በፊት የድርጅቱ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ዳባ ደበሌ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ቢሮውን ሲመሩ የቆዩ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር ንኪኪ ሳይኖራቸው አይቀርም በሚል በዓይነ ቁራኛ እየተጠበቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የአዳማ ከተማ ከንቲባና የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት በከር አቶ መላኩ ፈንታ ለእስር ከተዳረጉ በኋላ በዋና ዳይሬክተርነት ሲሾሞ ተቋሙን ይመሩታል ተብለው ይጠበቁ የነበረ ቢሆንም አሁን ፈተና ውስጥ የሚገኘውን ኦህዴድን ይታደጉት ዘንድ ጉምሩክን እንዲለቁ ተደርገዋል፡፡
አቶ ዳባ ደበሌ በኦሮሚያ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ አካላትም የኦህዴድ አባላት ዳባ የሚገኙበትን ሁኔታ ለማወቅ ለድርጅቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለአቶ ሙክታር አሊና ለአባዱላ ገመዳ ደብዳቤ መላካቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.