ከ አዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮች መብት አስከባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

Taxi aa
መንግስት ፍትሀዊ ጥያቄያችንን በሃይል ለማፈን ከሞከረ ከስራ ማቆም አድማ አልፈን በመኪኖችችን መንገዶችን በመዝጋት ማንኛውንም የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለማገት የተዘጋጀን መሆኑን ልናስጠነቅቅ እንወዳል

መንግስት ጉዳዩ የሚመለከተንን ሳያወያይ መብታችንን የሚጥሰና ስራችንን የሚይስተጓጉል ህግ አውጥቶ በስራ ላይ አውሏል። ይህ ህግ ገና በጥንሡ እያለ የወሬ ወሬ ሰምተን ከመንግስት ጋር ለመወያየት ጥያቄ ብናቀርብም አድማጭ አላገኘንም። ስለዚህም መብታችንን ለማስከበር እና አድማጭ ለማግኘት ከዛሬ ሰኞ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ጠርተን በተሳካ ሁኔታ መጀማርችን ይታወቃል።

አሁንም መንግስት ለአቤቱታችን አዎንታዊ መልስ ከመስጠት ይልቅ ወደ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ገብቷል። የታክሲዎች ታርጋ እንፈታለን፣ ሾፌሮችን እናስራለን፣ ባለንብረቶችን እናሳራለን እያለ ነው። እንዲህ አይነት ማስፈራሪያ መፍትሄ መሆን እንደማይችል ልንመክር እንወዳለን። ህጉን ለሶስት ወር እናዘገያለን የሚለውን ማታለያም እንደማንቀበል ልንገልጽ እንወደለን። መግስት በአስቸኳይ ይህንን ህግ ሙሉ በሙሉ በ አዋጅ ካልሻረ እና ያለአግባብ ንሮ የሚገኘውን የነዳጅ ዋጋ ከአለም ገበያ አኳያ እስካላስተካከለ ድረስ

1) በአዲስ አበባ የተጀመረው የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

2) በሀገሪቱ በሙሉ ያሉ ሾፌሮች አድማውን ይቀላቀላሉ።

3) መንግስት ፍትሀዊ ጥያቄያችንን በሃይል ለማፈን ከሞከረ ከስራ ማቆም አድማ አልፈን በመኪኖችችን መንገዶችን በመዝጋት ማንኛውንም የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለማገት የተዘጋጀን መሆኑን ልናስጠነቅቅ እንወዳል።

በዚህ ክስተት የተከበሩ ደንበኞቻችን ላይ ለደረሰው መጎሳቆል ከልብ እናዝናለን። ህዝቡ ላደረግነው መብታችንን የማስከበር ጥረት ቀና የሆነ ትብብርና ግብረ መልስ በመስጠት ከጎናችን እንደሚሆን ስለአረጋገጠልን ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን መብታችን እንደተከበረ በፍጥነት እና በተሻለ መልኩ ወደስራ በመመለስ እንደምንክሳችሁ ቃል እንገባለን።

አስተባባሪ ኮሚቴው

ፊርማ የማይነበብ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.