ግብጽ 1 ሚልዩን ዶላር በድርቁ ለተጎዱ ወገኖቻችን አበርክታለች

Sis(ሳተናው) ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅና ርሃብ ምክንያት እርደታ በመጠየቅ ላይ ለሚገኘው ለተባበሩት መንግስታት የአለም ምግብ ፕሮግራም የአንድ ሚልዩን ዶላር እርዳታ መለገሷን የፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ ይፋ አድርገዋል፡፡ ‹‹አስተዋእጾው የተገኘው በጣም ወሳኝ በሆነ ወቅት ነው፡፡በድርቁ ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን መንግስትና የአለም የምግብ ፕሮግራም አቅማቸውን በማሰባሰብ ያለውን ርዳታ ለመጨረሻ ጊዜ ለማከፋፈል በተዘጋጁበት ወቅት ግብጽ እርዳታውን ማድረጓ ትልቅ ትርጉም አለው››ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ከግብጽ በተገኘው የእርዳታ ገንዘብም ፕሮግራሙ 1.700 ሜትሪክ ቶን ምግብ፣የምግብ ዘይትና በከፍተኛ ደረጃ በድርቁ ለተጎዱ አካባቢዎች የህጻናት ምግብ በመግዛት እንደሚያከፋፍል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹የግብጽ መንግስትና ህዝብ በኢልኒኖ ምክንያት በኢትዮጵያ ሚልዩኖች ለችግር በመጋለጣቸው ሐዘን ተሰምቷቸዋል፡፡በዚህ ድጋፍ ማስተላለፍ የምንፈልገው መልእክትም አጋርነታችንና ድጋፋችንን ነው›› ያሉት የግብጽ አጋርነት ለልማት የተሰኘውን ኤጀንሲ የሚመሩት ዶክተር አዚም ፋሃሚ ናቸው፡፡
ከ10 ሚልዩን የሚልቁ ዜጎች በኢትዮጵያ ለከፍተኛ የምግብ እጦት በመዳረጋቸው የአለም ምግብ ፕሮግራም በይፋ እርዳታ የማስተባበር ስራ ጀምሯል፡፡እስከ ሚያዚያ ድረስም ምግብን ለተጎጂዎቹ ለማከፋፈል ፕሮግራሙ 350 ሚልዩን ዶላር ያስፈልገኛል ብሏል፡፡
የግብጽ መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራምን በተለይም በአገሩ ውስጥ ይደረግ የነበረውን የድርጅቱን እንቅስቃሴ ሲደግፍ ቆይቷል የሚሉት ጆን ከአገር ውጪ ለተከሰተ ችግር ይህን ያህል ከፍተኛ ገንዘብ ሲለግስ ግን የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ -ኦል አፍሪካ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.