ኢትዮጵያዊው በኮንቴይነር ውስጥ ተደብቆ ስዊዲን ገባ

1279

(ሳተናው) በስቶክሆልም የአርላንዳ አየር መንገድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ያረፈውን አውሮፕላን ዕቃዎችን ሲያራግፉ በኮንቴይነር ውስጥ ትናንት ማለዳ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝን ኢትዮጵያዊ ማግኘታቸውን የአገሪቱ ጋዜጦች ይፋ አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያዊው በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ጋዜጦች ወጣቱ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርቧል ብለዋል፡፡
የስቶክሆልም ፖሊስ ቃል አቀባይ ካሪና ስካግሊንድ ስደተኛው በህይወት ለመቆየት የቻለው የነበረበት ኮንቴይነር ያልታፈነ በመሆኑ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ስሙ ያልተጠቀሰው ኢትዮጵዊ በምን መልኩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አውሮፕላኑ መግባት እንደቻለ የተሰጠ ማብራሪያ ባይኖርም በ1980 የተወለደ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የአውሮፕላኑ ሰራተኛ ሲያገኘው በመጠኑ ተዳክሞ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል በማለት የፖሊሱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
አውሮፕላኑ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ስዊዲን ከማረፉ በፊት በቪየና ለሰዓታት አርፉ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን በአጠቃላይ የመጨረሻው ማረፊያው ለመድረስ 10 ሰዓት ከ25 ደቂቃዎች ወስዶበታል ተብሏል፡፡
‹‹ኮንቴይነሩ ከውጪው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አየር እንደነበረው በትክክል የሚያውቅ ሰው መሆን አለበት፡፡በዚህ ምክንያት በህይወት ለመገኘት በቅቷል››ያሉት ካሪና ስካግሪልድ ናቸው፡፡
በነሐሴ ወር 2007 የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ በተመሳሳይ መልኩ ሻንጣ ውስጥ ተደብቆ ስዊዲን በመግባት ጥገኝነት መጠየቁም አይዘነጋም፡፡ግለሰቡ በአዲስ አበባ የአየር መንገዱ ሰራተኛ መሆኑን መናገሩም ይታወሳል፡፡
ስዊዲናዊው ጋዜጠኛ ዩሃን ሊቭ ‹‹ራሳቸውን ለአደጋ በመስጠት የሚመጡበት መንገድ ያልተለመደ ነው፡፡ከአሁኑ በፊት ከሰማሁት በቀር እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም ለሁተኛ ጊዜ ነው››ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት በስፋት የሚረገጥባት በአምባገነን መንግሰት የምትተዳደር አገር መሆኗ በስዊዲን ይታወቃል፡፡በተለይም ሁለቱ ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች ማርክ ሽቢዬና ዩሃን ፒርሰን ከታሰሩ በኋላ አገሪቱ ትኩረት አግኝታለች፡፡
በ2007 በስዊዲን የጥገኝነት ጥያቄ ካቀረቡ ስደተኞች መካከል 1 ከመቶ የሚደርሱት ኢትዮጵያዊያን ነበሩ፡፡በዚህ አመት ከታዩ የስደተኝነት ጥያቄዎች መካከልም የግማሽ ያህሉ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡
ምንጭ ኤክስፕረስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.