120ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል  በዳላስ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

dallas1

የአድዋ ድል ጀግኖች አያቶቻችን ሃገራችንና ህዝባችን በነጭ ቁጥጥር ስር በባርነት እንዳይወድቅ አጥንታቸው ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው እልህ አስጨራሽ ውግያናተጋድሎ በማድረግ ድንበር ተሻግሮ የመጣው የፋሽስት ጣልያን ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ጥቁር ነጭን እንደሚያሸንፍ በተግባር ያሳዩበት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆንለመላው ጥቁር ነፃነት መሰረት ነው። ስለ አድዋ እንዲህ በቀላሉ ተነግሮ እሚያልቅ አይደለም። ለኢትዮጵያውያን የዛሬ ማንነታችን ውጤት የአድዋ ድል ነው።

ይችን ታሪካዊ ዕለት 120ኛውን ዓመት ለመዘከር እሁድ March 6, 2016 ፕሮግራሙ ያዘጋቸው የኢትዮጵያውያን ጉዳዮች ፎረም በዳላስ ሲሆን በእለቱ ብዙኢትዮጵያውያን ተሳትፈው ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተውታል። ፕሮግራሙ አድዋን የተመለከተ ዶክመንታሪ ለታዳሚው በማቅረብ ተጀመረ። ዶ/ር መስፍን ገናናውና አቶይርጋለም ጎበዜ(አገሬ ኢትዮጵያ) የእለቱ የክብር እንግዳ የነበሩ ሲሆን አቶ ይርጋለም ጎበዜ አድዋን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት የሰጡ ሲሆን ዶ/ር መስፍን ገናናው የአርበኛአያቶቻችን የአድዋ ተጋድሎ ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ንግግር አድርገዋል። የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የጋራ መረዳጃ ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሙሉጌታ ኮሚኒቲውን በመወከል ንግግር አደርገዋል። አጼ ሚኒልክና እቴጌ ጣይቱ የነበራቸው በሳል አመራር በሰፊው ተወስቷል።

አዳራሹ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ በጋሻና ጦር እንዲሁም የአጼ ሚሊክና እቴጌ ጣይቱ ባህላዊ አለባበስ ጨምሮ የሌሎች አርበኞች ባህላዊ የአለባበስ ስርዓት በለበሱ ተሳፊዎችደምቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የአጼ ሚኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ጨምሮ አድዋ ሲነሳ ሁሌም ስማቸው የሚነሱ አርበኞቻችን ፎቶግራፍ ሁሉንም ማግኘት ባይቻልም የተወሰኑትንተሰቅለው ነበር።

በፕሮግራሙ መሃል አድዋን የተመለከቱ ባህላዊ ጣዕመ ዜማ ያላቸው ሙዚቃዎች በዲጄ ዮናስ(ዩቶፒያ) የቀረቡ ሲሆን ከእንግዶችና ከታዳሚዎች ግጥም ቀርበዋል። የአጼሚኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ፎግራፍ ያለበት በኮሚቴው የተዘጋጀ ኬክ ተቆርሷል። በመጨረሻም የበዓሉ ተሳፊዎች ውይይት አድርገውና የፕሮግራሙ አዘጋጆችን አመስግነውየፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆነ።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!

የኢትዮጵያውያን ጉዳዮች ፎረም በዳላስ

dallas4

dallas 5 dallas 6 dallas 7 dallas 8
dallsa2 dallsa3

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.