በዱባይ ለምትገኙ ወገኖቻችን ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ | የሃገሪቱ መንግስት ይህን አዲስ ሕግ አውጥቷል

በማስረሻ መሐመድ

Dubaiበዓለማችን ላይ የትራፊክ አደጋ እጅግ አሳሳቢ እየሆኑ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

የትራፊክ አደጋ ከሚከሰትባቸው በርካታ ምክንያቶች ውስጥ ደግሞ እያሽከረከሩ ስልክ መጠቀም አንዱ መሆኑ መሆኑ ነው የሚነገረው።

ታዲያ ህይ ራስ ምታት የሆነበት የዱባይ ፖሊስም ይህንን ችግር ሊቀርፍ የሚችል አዲስ ህግ አውጥቻለው ብሏል።

ከዚህ ቀደም ዱባይ ውስጥ እያሽከረከሩ ስልክ መጠቀም በሀገሪቱ ገንዘብ 200 ድርሃም የሚያስቀጣ ነበር።

ታዲያ ይህ ቅጣት አሽከርካሪዎችን ከተግባራቸው ሊያስቆም አልቻለም የሚለው የዱባይ ፖሊስ፥ ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት ለመጣልም ወስኗል።

ታዲያ በውሳኔያቸው መሰረትም በዱባይ አውራ ጎዳናዎች ላይ እያሽከረከሩ ስልክ የሚጠቀሙ የሰዎች ከተያዙ በ1 ሺህ የሀገሪቱ ገንዘብ እንዲቀጡ የሚያደርግና ተሽከርካሪያቸውንም ለ1 ወር እንዲያጡ  የሚያደርግ አዲስ ህግን አውጥተዋል።

ይህም አሽከርካሪው በፈፀመው ጥፋት ለ1 ወራት ተሽከርካሪው እንዲታሰር የሚያደርግ ነው።

የዱባይ ፖሊስ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፥ ህጉ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መብራት እስኪለቃቸው በሚጠብቁበት ጊዜ እንኳን ቢሆን ስልክ መጠቀምን የሚከለክል ነው።

በእንዲህ አይነት ስፍራ ላይ ስልክ ሲጠቀሙ ቢገኙም አሽከርካሪዎቹ ህግን በመተላለፋቸው ተመሳሳይ ቅጣት ይጠብቃቸዋልም ብለዋል።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት በዱባይ 49 ሺህ 643 ሰዎች በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የሞባይል ስልክ በመጠቀማቸው ተይዘው ቅጣት እንደተላለፈባቸው የሀገሪቱ ፖሊስ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ታዲያ እንዲህ አይነቱ ህግ በለሌሎች ሀገራትም ቢለመድና በስፋት ጥቅም ላይ መዋል ቢጀምር በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ ያስችል ይሆን?

ምንጭ፦

www.emirates247.com