የኢትዮጵያ መንግስት ሶስት ሚልዩን ብር የመደፈር ጥቃት ለደረሰባት ሴት እንዲከፍል ተወሰነበት

rap

(ሳተናው) የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት የመደፈር ጥቃት የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት መንግስት መብቷን ሳያስከብር በመቅረቱ በካሳ መልክ 150.000 ዶላር (ሶስት ሚልዮን ብር) እንዲከፍላት መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
በ1995 ጂማ ንጉሴ አብረው የተባለ ግለስብ የ13 ዓመትን ታዳጊ ደፍሯል የሚል ክስ ቀርቦበት ብይን ተሰጥቶት ነበር፡፡ነገር ግን አቀቤ ህግ ‹‹ልትደፈር የምትችለው ድንግል የሆነች ሴት ናት ተደፈርኩ ባይዋ ግን ድንግል መሆኗን አላሰረዳችም››በማለት ይግባኝ በመጠየቁ ፍርዱ እንዲነሳለት ተደርጓል፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ለይግባኙ የተሰጠው ውሳኔ የአገሪቱንም ሆነ አለም አቀፍ ህግጋትን የሚቃረን መሆኑን ይገለልጻሉ፡፡
በ1999 እኩልነት አሁን (Equality Now) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ፍትህ ተጓድሏል በማለት ጉዳዩን ለአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቀረበው፡፡
ከዘጠኝ አመታት በኋላ በጋምቢያ ተቀማጭነቱን ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ፍርድ ቤት ኢትዮጵያ የታዳጊዋን ክብር፣እኩልነትና ተገቢ ፍትህ የማግኘት መብት አላከበረችም በማለት ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡የተወሰነላት ገንዘብም መብቷ በፍርድ ቤት በድጋሚ የተጣሰ በመሆኑ በካሳ መልክ እንዲከፈላት ተወስኗል፡፡
ጉዳዩን ወደአፍሪካ ፍርድ ቤት የመራው እኩልነት አሁን የተባለው ተቋም ከውሳኔው በኋላ በሰጠው አስተያየት ‹‹ የተላለፈው ውሳኔ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ተገቢ መልእክት ያስተላልፋል››ብሏል፡፡
በ1993 መታፈኗ ለፖሊስ በቤተሰቦቿ አቤቱታ ከቀረበ በኋላ በተደረገ ፍለጋ ስትገኝ መደፈሯ ታውቆ የድርጊቱ ፈጻሚም ለእስር ተዳርጎ ነበር፡፡ ግለሰቡ በዋስ እንዲለቀቅ ከተደረገ በኋላም በድጋሚ አፍኖ ወስዷታል፡፡
ለወር ያህል ደብዛዋ የጠፋው ታዳጊዋ እንድትቀመጥ ከተደረገችበት ቤት በመጥፋት ወደቤተሰቦቿ ተመልሳለች፡፡ግለሰቡ አፍኖ ባስቀመጣት ወቅትም በሃይል በወረቀት ላይ ስሟን በመጻፍ እንድትፈርም በማድረግ ክስ በቀረበበት ወቅት በስምምነት ጋብቻ መፈጸሟን ለማሳየት ተጠቅሞበታል፡፡
በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎችም ህጻናትን ያለ ዕድሜያቸው መዳርና ጠልፎ በሀይል መውሰድ እንደባህል ይቆጠራል፡፡
ጂማ በ1995 ለሁለተኛ ጊዜ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ ከአራት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ፍርድ ቤት ቀርቦ የአስር ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር፡፡ነገር ግን በይግባኝ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሮላቸው እንዲለቀቁ ቢደረጉም እኩልነት አሁን የተባለው ተቋም የድንግልና መኖር ወይም አለመኖር ለመደፈር እንደ ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ አይገባውም በማለት አቤቱታውን ለአፍሪካ ህብረት ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡
ከህብረቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላም የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ተቋም የመደፈር ጥቃት ለሚደርስባቸው ኢትዮጵያዊያን የአገሪቱ ህግ ከዚህ ውሳኔ በመማር የተሻለ ጥበቃ ያደርጋል የሚል እምነት እንዳደረበት አስታውቋል፡፡በአሁኑ ወቅት በ20ዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘዋ የቀድሞዋ ታዳጊ ደህንነቷ በተጠበቀበት ሁኔታ በዘመዶቿ ቤት በመሆን ትምህርቷን እየተከታተለች ትገኛለች ብሏል፡፡
ምንጭ ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.