በደቡብ ሱዳን የወታደሮች ደሞዝ ሴቶችን መድፈር ነው

sudan(ሳተናው)የደቡብ ሱዳን ወታደሮች አካል በመሆን ከአማጺያን ጋር ይዋጉ የነበሩ ሚሊሻዎች ደሞዝ የሉ ጎሳ ተወላጅ የሆኑ ሴቶችን መድፈር እንደነበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት አጋልጧል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ያደረጉ ባለሞያዎች ባለፈው አመት ብቻ በነዳጅ ዘይት ሀብት በበለጸገችው ክልል ብቻ 1300 ሴቶች ተደፍረው ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ ሪፖርትም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ከ60 የሚበልጡ ጎልማሶችንና ልጆችን በአንድ ኮንቴይነር ውስጥ በመንግስት ኃይሎች ታፍነው መገኘታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡መንግስት ወታደሮቹ ሲቪሎችን ኢላማቸው እንዳላደርጉ በመጥቀስ ምርመራ ማድረግ ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡
የሳልቫኪር መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቴኒ ዌክ ለቢቢሲ በሰጡት አስተያት ‹‹የአሰራር ደንብ ያለን በመሆኑ በራሳችን መንገድ ጉዳዩን እየመረመርን እንገኛለን››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር የሆኑት ዚያድ አል ሁሴይን ‹‹በደቡብ ሱዳን የምንመለከተው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የአለማችን ትልቁ ሊሰኝ የሚገባው ደረጃ ላይ ይገኛል››ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለቤቷ ፊት ለፊቷ ከተገደለባት በኋላ አንዲት እናት የ15 ዓመት ልጇን 10 ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደፍሯት መመልከቷን ተናግራለች፡፡
የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ የመንግስት ወታደሮች ሴቶችን በማፈን መድፈራቸውንና የሲቪሎችን አካላት እንደሚቆራርጡ በመጥቀስ ተቃዋሚዎችም ተመሳሳይ ወንጀል ይፈጽማሉ ብሏል፡፡
የአምንስቲ ኢንተርናሽናል አጥኚዎች በኮንቴይነር ውስጥ ታፍነው የነበሩ ሰዎች ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በሊር ከተማ መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከ2005 ጀምሮም በደቡብ ሱዳን በሺዎች የሚቆጠሩ ሲገደሉ ሚልዩኖችን ተፈናቅለዋል፡፡ብዙዎችን የመንግስት ወታደሮች በማሰቃየት እንደሚገድሏቸው የሚናገሩት የአምንስቲው ላማ ፋኪህ ‹‹ከህግ አግባብ ውጪ በህገ ወጥ መንገድ የሚደረጉ ግድያዎች የግዴታ ምርመራ ሊደረግባቸው ይገባል››ብለዋል፡፡
ምንጭ ቢቢሲ