ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በመላው የኖርዌይ ከተሞች በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

የወያኔ መንግስት በህዝባች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋና ሰብሀዊ ጥሰት በመቃወምና የኖርዌይ መንግስት ለዚህ አንባገነን ስርሃት የሚያደርገውን ድጋፍ በመቃወም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  በመላው የኖርዌይ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ::

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ  የጠራው ይህ  ሰላማዊ ሰልፍ በኦስሎ: በበርገን :በትሮደያም: በስታቫንገርና በሌሎችም ከተሞች የተካሄደ ሲሆን   ባሁን ሰሀት በአገራችን ኢትዮጵያ  በተለይም በኦሮሚያ: በአማራ: በጋንቤላና በኮንሶ ከፍተኛ ህዝባዊ ትግል እየተደረገ መሆኑንና ይህንንም ተከትሎ የወያኔ ሰራዊት ቁጥራቸው በርከትያሉ ንፁሀን ዜጎችን መግደላቸውን ማቁሰላቸውና በርካቶችም ለስደት መዳረጋቸውን ለኖርዌይ መንግስት ተወካይ አሳውቀዋል::

ተያይዞም የኖርዌይ መንግስት ከአረመኔው የወያኔ ስርሃት ጋር የሚያደርገውን ትብብር ሊያጤኑት ይገባል ያሉ ሲሆን〉በስታቫንገር የሚኖሩ አንድ ታዳሚ በሀገራችን ተራብን: ተደበደብን: ታሰርን ብሎም ተገደልን ከዚህ በዋላ ምን ቀረን በማለት በምሬት ተናግረዋል;; በሀገራችንም እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየን በሰው ሀገር ስደት መተንም መኖር አልቻልንም  የኖርዌይ መንግስት ለዚህ አንባገነን ሰው በላ ስርሀት አሳልፎ እንዳይሰጠን በማለት ተማፅነዋል::

በመጨረሻም የኖርዌይ መንግስትና ሚዲያው የረሱት በወያኔ እስርቤት እየማቀቀ የሚገኘው የኖርዌይ ዜግነት ያለው አቶ ኦኬሎ አክዋይ እንዲፈታ የተጠየቀ ሲሆን  የኖርዌይ መንግስትም ጉዳዩን እንዲከታተልም አሳስበዋል::

dsc_0316 1914736_663401500466257_3472448823215670767_n (1) 1914736_663401500466257_3472448823215670767_n