አሰደንጋጭ ዜና – ኢቦላ መሰል በሽታ በኢትዮጵያ አሶሳ መከሰቱን አዲስ አድማስ የአካባቢውን የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጥቀሷ ዘገበ ።

አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል
የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታው ኢቦላ አይደለም ብሏል
በሽተኞች ላይ ደም ማስመለስና ማስቀመጥ ተስተውሏል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ በሁለት ሰዎች ላይ መከሰቱንና አንደኛው መሞቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታዬ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን የኢቦላ በሽታ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ አልተከሰተም ብለዋል፡፡

ebolaየተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ በሚገኘው ባምባሲ የስደተኞች ጣቢያ በሽታው ተከስቷል ሲሉ ያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊው፤ ለጊዜው በትክክል ምንነቱ ያልታወቀው በሽታ የተከሰተው ከስደተኞች ጋር ምንም አይነት ንክኪ በሌለው የአሶሳ ከተማ መንደር 47 በሚባል አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በህክምና ባለሙያዎች የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል በተባለው በዚህ በሽታ የተያዙት ሁለት ግለሰቦች ላይ የታየው ምልክት ደም ማስመለስና ማስቀመጥ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሃብታሙ፤ በሽተኞቹ ለብቻ ተገልለው በጥንቃቄ እንዲታከሙ ተደርጓል፣ የአንደኛውን ህይወት ማትረፍ ባይቻልም ሌላኛው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡
የኢቦላ በሽታ ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ጋርም ሊመሳሰል ይችላል ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ነገር ግን በህክምና ባለሙያዎች በሽታው ኢቦላ አለመሆኑ ተረጋግጧል፤ በሽታው የምግብ መበከል ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል ብሏል፡፡

በድንበር አካባቢ በሽታው ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የጠየቅናቸው ኃላፊው፤ ሱዳን ውስጥ በሽታው ስለሌለ ስጋት የለብንም ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በሽታው ኢቦላ ነው በሚል እንዳይደናገጥ በክልሉ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትናንት ጠዋት ቀርበው በሽታው ኢቦላ አለመሆኑን ማስረዳታቸውን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪም ግብረ ሃይል በማቋቋም ምንነቱ በትክክል ያልታወቀውን በሽታ ለማጣራት ባለሙያዎች የተከሰተበት ቦታ ድረስ በመሄድ የማጣራት ስራ መስራታቸውንና ኢቦላ በክልሉ የትኛውም አካባቢ እንዳልተከሰተ ማረጋገጣቸውን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አህመድ አማኖ፤ በሃገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ኢቦላ አለመከሰቱን ከየክልሎች በሚሰበሰቡ መረጃዎች መረዳት መቻሉን ለአዲስ አድማስ ገልፀው፤ ምናልባትም ከሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ትኩሳት፣ የአፍንጫ መንሰር ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል፡፡ አሶሳ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲዎች የተሰራጨውም ትክክለኛ መረጃ አይደለም ብለዋል ኃላፊው፡

ምንጭ አዲስ አድማስ

2 COMMENTS

  1. What was going on there? Are they friends? Why they were together? Every story has two side, all we have seen is, the white dude swinging, and brother taking punchs. We’re missing one side of the story. And btw good job bro, at least you tired to escape the situation, u didn’t just lay n take all punchs

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.