መሪያችን አውነ ከሆነ – አስገደ ገብረስላሴ

የሀይለማርያ ደሣለኝ ከማክሠኞ የቀጠለ:

ኣራት ኣንኳር ነጥቦች ጥለዋል

1ኛ መንግሥታችን በመልካም አሥተዳደር ነጻና ግልጽ መረክ መክፈት አለበት!!
2ኛ  ህዝብ ለማያምንበት ነገር ነጻነት አግኝቶ በአደባባይ ወጥቶ መጮህ አለበት :: መንግሥትም የሚያዳምጥ ጀሮ መሥጠት አለበት!!
3ኛ  ሀዝብ በነጻነት እንዲታገል እድል ይሠጠው በኣመነበት ይሂድ  ካላመነበት በእምነቱ ይጓዝ !!
4ኛ ህዝብ መጓች እና  ጠንካራ ታጋይ መሆን አለበት !! ከዛም በዘለለ ተደራጅቶ ለለውጥ መንቀሣቀሥ አለበት !! ብ    ብለዋል :: ሀይለማርያም ደሣለኝ ምነው   90  ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝብ የህልም ማርና ወተት  ባያጠጡት ምነው በኣመሪካ  :  በአውሮፓ  በከናዳ  ያለው የዜጎቻቸው ነጻነት አምጥተው ህወሓት ኢህአደግ በሥለጣን እያለ ሊደረግ የመይችል: በመቃብሩ ካልሆነ በሥተቀር ::አምጥተው ቢያንሣፉፉን በመሬትም በሠማይም ሀጢያት አይሆንበትዎን  ?

በፍጹም በህወሓት ኢህኣደግ  መንደር የሀይለማሪያ ደሣለኝ አባባል  በሬም ወለደ እንደ ማለት  ነው ::

Asgede
አቶ አስገደ ገብረስላሴ

አቶ ሀይለማርያም ደሣለኝ    እነዛ አራት ነጥቦች ለህዝቦች ከሞላ ጎደል  ቢማሉ ንሮ በአሁኑ ጊዜ ያሉ ጥያ ቄዎች የግለሠው መብት መጠበቅ እና የመሬት የግል ባለቤትነት ቢጨመርበት :  ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች  ለድርድር በቀረቡ ነበር::
በዚያን ጊዜ ግን የህወሓት ኢህአደግ አማራር እና ተላላኪ ካድሬዎች ባንው ያድራሉ:: ምክንያቱም ዜጎች አደባባይ ወጥተው ለነጻነታቸው ከተማጎቱ ከጮሁ  በናጽነተ ከታገሉ አንባገነኑ የአቤታዊ ዲሞክክራሢ  ሞተዋል መለት ነው:: እሡ ከሞተ ደግሞ የህወሓት ኢህአደግ አማራር እና አሥተሣሠባቸው እና በሊሣቸው ተቀብረዋል መለት ነው ::
እኔ የገረመኝ ግን ይህ ሁሉ የህዝብ ጥያቄ የሚመልሥ አነጋገር  ተናግረው የት ለያድሩ ናቸው:: እኔ እንደሚመሥለኝ የህዝብ  ሥሜት ገፍቷቸው የተናገሩት ሀሣብ ነው: ወይ ከደሙ ነጻ እወጣለሁ ብለው ወደ ሠብአውነታቸው እየተመለሡናቸው:: ወይ ወደውጭ መማላለሥ ሥለኣበዙ  በዲሞክራሢ ተጠምቀው ይሆናሉ ጥርጣሬ ይዤ ነበር::የእኔ ጥርጣሬ ግን  ትክክል አልነበረም::

ምክንያቱም የሀይለማርያም አነጋገር ሀቀኝነት ቢነረው  ንሮ ያሁሉ ሠላማዊ ንግራቸው   ሢሠማ ማንም ሠው በነጋታው ዜጎች የሚገድለው  ያለው ወታደር በነጋታው ግድያ ይቆማል የሚል ግምት ያሣድርራል ግን ደግሞ እሥከዛሬ መጋቢት 09/07/2008 ዓ  /ም በኦሮሞ እምቢ ለመብታችን ያሉ  ወጣቶች   በጥይት እየተቀሉ እንመለከታለን:: ሥለዚህ የሀይለማርያም ደሣለኝ  የዲሞክራሢ  ጳጳሥ መምሠል አሥመሣይ ከመባል  ሌላ ተርጉም ሊሠጠው አይችልም:: ኣቶ ሀይለማርያም እንዳሉን ከሆነ ህዝብን እንዳይናገር እንዳያይ እንዳይእንቀሣቀሥ   በሀገሩ  ነጻ ሆኖ እዳይኖር  ጨምድዶ ኣፍኖ ይዞ ያለ የአንድ ለአምሥት የሥለላ መዋቅራቸው ማፍረስ ኣለበቸው:   ሁሉም  ነጻነት ሥለጠየቁ በወህኒ ቤት እየማቀቁ  ያሉ የፓርት መሪዎች  አባሎቻቸው ጋዜጠኞች ደጋፊዎች   በአጠቃለይ ወሀ ቀጠነ ምክንያት እፈጠራችሁ  ያሠራችኋቸው  ዜጎች  ይፈቱ:: ሌላ  የሀዝብ የምርጫ ድምጽ ወሮ በምርጫ ሽፋን በፓርላማ አዳራሽ የመሏው   ቅለብ እያንቃላፋ  ያለው  ቅምጥ  ወይ የካድሬ  መሠረታዊው ድርጅት  ፈርሦ ሀቀኛ  ህዝባዊ ምርጫ መካየድ አለበት:: ይሀ ካልሆነ  የሀይለማርያም ደሣለኝ  ዲሥኩር  ባዶ ነው::

ሌላ የአቶ ሀይለማርያም ደሣለኝ የሀገራችን መሁራን    በሥመ ሙሁራን እና ተመራማሪዎች ብለው  ከ500በላይ የሠበሠቡዋቸው የኢትዮጱያ ህዝብም ትእዝብት እነደአሣረፈበት የህወሓት  ኢህአደግ  አባላት እና ተላላኪ ካድሬዎች መሆናቸው ተገንዝቧል ::
ጠ/ ም/ ሀይለማርያም ደሣለኝ በአሁኑ ጊዜ ያለው በሀገራችን ያለ የፓለቲካዊ  አለመረጋጋት መፍትሄ ለማግኜት   ከተፈለገ   ቡቁ ሙሁራኖች ተመራማሪዎች  በመሣተፍ ብቻ  ሣይሆን በአማራር  ጭምር መውጣት አለበቸው የሚል ሀሣብ ማምጣት ወይ ማመንጨት ነበረባቸው:: ግን ጌቶቻቸው አይፈቅዱላቸውም እና:: ሥለዚህ በሥብሠባው  የነበሩ በሥመ ሙሁራን የተሠበሠቡ ሙሁራን ተብየዎች ባገር ውሥጥም በሥደት ያሉ ሙሁራኖች እና በፖለቲካ ምክንያት ተሠድደው በባእድ አገር ያሉ ሊህቃን አይወክሉም:: በመሆኑም የሀይለማርያም ዲሥኩር  በዲንጋይ እንደፈሠሠ ውሀ ይቆጠራል :  :
በአጠቃለይ የሀይለማርያም ደሣለኝ አነጋገር ከወዲሁ በተራ  አርሦ አደር ሣይቀር   እየተተቸ  ነው::

ሀይለማርያም እና  ሠርአታቸው  በቅን መንገድ ቢነሡ ንሮ የመሠረታዊ ድርጅት  ሙሁራን ተበየዎች   ሥብሠባ መሆኑ ቀርቶ የተቃዋሚ ፓለቲኮኞች  ባገር ውሥጥና በውጭ ያሉ ሙሁራን ተመራማሪዎች   ጋዜጦኞች  ነጻ ማህበራት    የሀይማኖት  አባቶች  ተሞክሮ  ያላቸው ግለሠወች   ከገጠርም ከከተማም ያገር ሽማግሌዎች     ሠብሥባችሁ ብታነጋግሩ ሀቀኛ መፍትሄ ታገኙ ነበር :: ካለበለዝያ በሥመ ሙሁር ሀዝብን ለመታለል  ካድሬ በመሠብሠቡ ከአፍ ወደጀሮ ከጀሮ ወደ አፍ ከማዳመጥ ውጭ ሌላ ትርጉም አይሠጠውም ::በመሆኑም  አቶ ሀይለማርያም ደሣለኝ  አሁንም የተናገሩት ሁሉ ውሥጠ ሤራው የማይረዳ   ዜጋ  አንድ እርምጃ   ወደፊትእንደተራመዱ  ቢረዳውም  መላው ሀዝብ ገን አልተቀበለዎትም:: ሥለሆነ አሁንም ቆም ብለው አሥበውበት ቀና መንገድ ይፈልጉ :: ማሣለፍ የሚከለክልዎ ጋሬጣ ካለ  ከሀዝብ ሆነው  አደባባይ ወጥተው ሞጮህ ነው መፍትሄው::
ከአሥገደ ገብአሥላሤ መቀለ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.