ኢየሩሳሌም በቤተ እስራኤላዊያኑ የተቃውሞ ሰልፍ ተናጠች

ethiopian

(ሳተናው) ኢትዮ – ቤተ እስራኤላዊያን በኢየሩሳሌም በዛሬው ዕለት የአገሪቱ መንግስት በአዲስ አበባና በጎንደር የቀሩ ቤተእስራኤሎችን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ በመቃወም አደባባይ መውጣታቸው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙት ቤተ እስራኤላዊያን በግዴታ ክርስትናን እንዲቀበሉ መደረጋቸውን የጠቀሰው የዜና ምንጩ ሰልፈኞቹ የወገኖቻቸውን ፎቶግራፎች በመያዝ መንግስት አቋሙን በመቀየር ወደ እስራኤል ለመምጣት የሚጠባበቁትን ቀሪዎቹን 9.000 ቤተ እስራኤላዊያንን በአስቸኳይ በማምጣት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያገናኛቸው መጠየቃቸውን ዘግቧል፡፡

በየካቲት ወር መንግስት ቤተ እስራኤላዊያኑን ከኢትዮጵያ ለማምጣት የነበረውን ፕሮግራም ማገዱን መግለጹ አይዘነጋም፡፡የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ሲያቀኑ ‹‹የካቢኔዎቹ  ውሳኔ ስራ ላይ መዋል የለበትም››፣ ‹‹ልዩነት ይወገድ››፣‹‹በይሁዲዎች መካከል ልዩነት የለም››፣‹‹አድልኦና ማግለል ይቁም››የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡

የእስራኤል ሴኔት አባላትና የሊኩድ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቭራም ናጎሳና ዴቪድ አምሳለም እንዲሁም የጽዩኒስት ህብረቱ ሬቪታል ስዊድ ሰላማዊ ሰልፉን መቀላቀላቸውም ተሰምቷል፡፡ሁለቱ የሴኔት አባላትም ላለፉት 10 ቀናት ተቃውሟቸውን ለማስመዝገብ ሲሉ በሴኔቱ ስብሰባ ላይ አለመሳተፋቸው ታውቋል፡፡

የበጀት እጥረት አጋጥሞኛል ያለው የኔታናያሁ መንግስት የያዝነው ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ከኢትዮጵያ ህመምተኞች፣በዕድሜ የገፉና ረዳት የሌላቸውን 500 ቤተ እስራኤላዊያንን ብቻ መርጦ እንደሚያመጣ በመግለጽ ቀሪዎቹን በጀት ሳገኝ በ2017 እወስዳቸዋለሁ ማለቱም ተነግሯል፡፡

ምንጭ ሃርቴዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.