የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነት ለጊዜው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

b6f280c18cd972981c97040b9b2f757b_Lአዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል አስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ረቂቅ አዋጁ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተጠሪነታቸው ከፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳይ ሚኒስቴር ስር እንዲወጣ የሚያደርግ ነው። በጥናት ላይ ተመስርቶ እስከሚወሰን ድረስ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን በረቂቅ አዋጁ ተገልጿል። የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ራሱን ችሎ በፌደራል ደረጃ እንዲቋቋም የሚያደርግም ነው።

ይህም በአዋጅ ለፍትህ ሚኒስቴር ተሰጥቶት የነበረውን በአንቀጽ 16 የተጠቀሰው ስልጣንና ተግባርም ለሚቋቋመው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲሆን ያደርጋል። የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽንም ተጠሪነቱ በቀጣይ ለሚቋቋመው የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደሚሆን ነው በረቂቅ አዋጁ የተገለጸው። በክልሎች አካባቢ እንዲሁም በሃይማኖት ተቋማት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ጨምሮ የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የፌደራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ተግባራት ናቸው።

ይሁን እንጅ የፌደራል ፖሊስ እና የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተጠሪነታቸው ለሚኒስቴሩ የተሰጠ ነበር። ከዚህ አንጻር ተቋማቱ የሚያከናውኑት ተግባር እና ከሚኒስቴሩ ጋር ያላቸው የተግባር ትስስር የጠበቀ ባለመሆኑ፥ ሁለቱ ተቋማት ተጠሪነታቸው አግባብነት ላለው አስፈጻሚ አካል ወይም ተቋም እንዲተላለፍ በመንግስት ታምኖበታል። ይህን ተከትሎም በዛሬው እለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል አስፈጻሚ አካላትን ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅን ጨምሮ ተዛማጅነት ያላቸው አራት ረቂቅ አዋጆችን ተመልከቷል። የፌደራል ፖሊስም የሃገርን ደህንነት በማስጠበቅ የሽብር ወንጀልን እየተከላከለ በመሆኑ እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠንቶ እስከሚወሰን ድረስ ተጠሪነቱ እንዲቀየር ተደርጓል።

የተቋማቱ ተጠሪነታቸው መቀየር እየተሰራ ያለውን ስራ ለማቀላጠፍ እንደሚያግዝ ነው የተገለጸው። ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጆቹ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለህግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

በበላይ ተስፋዬ / fanabc.com

ያው ሰሞኑን እንደሚታወቀው ብአዴን እና ህወሃት በወልቃይት ጉዳይ ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ነው።

አሁን ችግሮቹ ብሶባቸው አንዳንድ አከባቢ ላይ ህዝቡ መሳሪያ በመያዝ ከልዩ ሃይል ጋር እየተታኳሰ እና መንገድ እየዘጋ እንደሆነ በማህበራዊ ሚድያው ሥገለፅ ነበር።ይህ ሁሉ በሆነበት ሁኔታ ፍዴራል ፖሊስ ተጠርነቱ በፍጥነት ከፌደራል ጉዳይ ሚንስትር ( ከብአዴን ) ሥር ወጥቶ በብዙ የህወሃት አማካሪዎች ወደ ተከበቡት ጠቅላይ ሚንሥትር ሥር እንድገባ ተደርጓል።ያው ለደህንነት ጉዳይ አማካሪው ለአለቃ ፀጋዬ በርሄ ተጠር እንድሆኑ ተደርገዋል ማለት ነው።በጣም የገረመኝ ላለፉት 10 ዓመታት ለፌደራል ጉዳዮች ተጠር የነበረው መስሪያ ቤት አሁን ወደጠቅላይ ሚንስትሩ ሥር ለመዘዋወር ጥናቱን እንኲን ለማጠናቀቅ ድንገተኛ ሆኖ ሥለተገኘ በጊዝያዊነት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ተጠር እንድሆን ተደርጓል ይላል።

ያው ህወሃት ያስቸገሩትን ኦህዲድን ( ልክ ገብቷል) እና ብአዴንን ልክ እያስገባ ነው ።ህወሃት ባቡሩን በፍጥነት እያሽከረከረ ነው።ኦህዲድ ፍጥነቱን መቋቋም አቅቶት ወርዶል። ብአዴንም መውረዱ የሚቀር አይመስልም።ዱሮስ ልጅ ይሮጣል እንጅ አባቱን አይቀድምም።

Dereje Gerefa Tullu

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.