ወልቃይት ጠገዴ ዛሬ – አዲ ረመጽ

sisay
አቶ ሊላይ ብርሃኔ

አቶ ሊላይ ብርሃኔ ተገድለዋል የሚሉ ግምቶች በርክተዋል፡፡ ከጎንደር እና ከኹመራ ጳጳሳት መጥተው የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ከመንግሥት አካላት ጋር (ከሁለቱም ክልሎች ከተውጣጡ) ድርድር ላይ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለከታሉ፡፡ ዳንሻ ስልክ አይሰራም፡፡ ውኃ ከአሽሬና ከአርማጭሆ መኪናዎች በመሸከም ለተቃውሞ ለወጡ ሰዎች ሲያቀብሉ ውለዋል፡፡

የታሰሩ ሰዎች አርባ ኹለት ደርሰዋል፡፡ የዳንሻ ባለሀብቶች ታስረዋል፡፡ ብዙ የሕወሓት ባለሀብቶች ደግሞ ሐብታቸውን በማሸሽ ላይ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የዳንሻ እና አዲ ረመጽ ስልክ ስለማይሰራ ከጠገዴ ቅራቅርና ሶሮቃ አካባቢ ነው መረጃ ለመሰብሰብ የሞከርኩት፡፡

በነገራችን ላይ አዲ ረመጽ የተሰየመው በትግሬዎች ነው፡፡ ከተከዜ ማዶ ያለ መስፍን (የመስፍኑን ስምና ዘመን እመለስበታለሁ) ከወልቃይቶች ጋር መስፍናዊ ጦርነት ይጀምራል፡፡ ተከዜን ተሻግሮ የደጀናን አካባቢ እንዲሁም አሁን አዲ ረመጽ ያለበትን አካባቢ በቀላሉ ይይዛል፡፡ በዚህ ጊዜ ወልቃይቴዎች አንድም ሰው እንዳይቀር አድርገው ይፈጇቸዋል (በቀደሙት ዘመናት እንደነበረው ሁሉ)፡፡ በዚህ ጦርነት አምልጦ የሔደ የተከዜ ማዶ ሰው ‹‹አዲ ረመጽ›› ብሎ ሰየመው፡፡ አዲ ማለት አገር ሲሆን ረመጽ ደግሞ ረመጥ ማለት ነው፡፡ በአጭር አማርኛ የኃይለኞች (የሚፋጁ) ሰዎች አገር እንደማለት ይሆናል፡፡

አዲ ረመጽ- የእሳቶች አገር- ወልቃይት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.