በመቐለ ከተማ የባለ ባጃጆች ኣድማ 3ተኛ ቀኑ ይዟል – አምዶም ገብረስላሴ

1958064_216530522038147_374131675928793707_nየመቐለ ከተማ ህዝብ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ኣጋጥሞታል።
ዛሬ ጥዋት ኤፍ ኤም መቐለ (FM Mekelle ) የሰራው ዜና

* “ባለ ባጃጅ ማህበራት የይቅርታ ደብዳቤ ኣስገቡ” ኣለ ወዲ ሓየሎም የመቐለ መንገድ ትራንስፖርት ሓላፊ።

* “ባጃጅ የድሃ ኣገልጋይ ናቸው ተሎ ወደ ስራ ቢገቡልን” ኣንድ ነብሰጡር ሴት

* “መንግስት ከ ባለ ባጃጅ እልኽ ሊጋባ ኣይገባም ተሎ ወደ ስራ ይመልስልን” ኣንድ ኣባት ኑዋሪ።

የዜናው ርእስ “የመቐለ ኑዋሪዎች በትራንስፖርት መቸገራቸው ገለፁ። ” ይላል።

የሓላፊዎግ መልስ
“ተዋቸው ዕቁብ መክፈያ ሲያጡ በሶስተኛ ቀናቸው ሳይወዱ በግድ ሮጦው ወደ ጉያችን ይመለሳሉ”
ወዲ ሓየሎም የመንገድ ትራንስፖርት ሓላፊ

936633_1010884439003212_697892118025100849_n* “ኣስርቦ መግዛት” የሚል ፖሊሲ ይኸው “ዕቁብ መክፈያ ሲያጡ ይመለሳሉ” እያሉ በድህነቱ እየተሳለቁበት ነው።

ይኸው ህዝቡ በትራንስፖርት ችግር ሰዎች ህሙማን በየመንገዱ እየወደቁ ነው።

በምስሉ የምታይዋት እናት ኣራስ ስትሆን ወደ ህክምና መጓጓዣ ኣጥታ በትግራይ ቲቪ( Tig_TV) በቅጥያ ሱሙ ቶግ ቲቪ መንገድ ዳር ወድቃለች።

መንግስት መመርያው በኣፋጣኝ ኣስወግዶ ባጃጆች ወደ ስራ ሊመልሳቸው ይገባል።

ሓላፊዎቹ በቪ 8 መኪና እየተጓዙ ህዝቡ ባጃጅ ሊነፍጉት ኣይገባም።

‪#‎Bajaj_Protest‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

 

ከአሥገደ ገብረሥላሤ መቀለ

የመቀሌ የባጃጅ ባለንብረቶች እና 1600 የባጃጅ ሽፈሮች የመብት ጥያቄ ለትግራይ ሀዝብ ብለውም ለመላው የኢትዮጱያ ሀዝቦች እንደ ትልቅ ትንሠኤ ሙውታን ይቆጠራል::

በትግራይ ክልል 25 ዓመት ሙሉ ተርቦ እያለ ውሀ ጠምቶት እያለ :ፍትህ መልካም አሥተዳደር አጥቶ እያለ : መሪዎቹ ነጻሆኖ እንዳይመርጥ አንዳይናገር እንዳይጽፍ ታፍኖ አያለ : በነጻ እንዳይ ደራጅ አንደጠላት እየተመለከቱት እያለ: እሥከ አሁን አንድ የተቃውሞ ነጸብራቅ ካሣዬ በድህንነት በወታደር በመሪዎች እየተደቆሠ ሠለመጣ በሢኦል ንሮ እያለ ጥሩ ነው ያለሁ : ለሞሞት እያቃሠተ እያለ ድሀና ነኝ እያለ እሥከ ዘሬ ቆይተዋል::

አሁን ግን ሠው አፍነው ቢያፉኑት ፍጡር ነው እና :ዛሬ ከዘመናት አፈና በኋላ የመቀሌ የባጃጅ ሽፈሮች እና ባለንብረቶች ለመብታቸው አድማ ማሥነሣት ለሁሉም ጭቁኖች የትግራይ ህዝብ ትልቅ አብነት እና አንድ እርምጃ ወደፊት ነው:: ይህ ተቃውሞ ያሠጋቸው የህወሓት አንባ ገነኖች መሪዎች ከባጃጅ ሽፈሮች አድማ በሥተ ጀርባ አንድ ነገር አለ ብለው በመሥጋት መቀለ በፈደራል እና በክልሉ ለዩ ሀይል በእግረኛ ወታደረ በፓትሮል መኪኖች ሢኑጣት ወለዋል ::

ይህ የሚያመለክተው ጭቁኑ የትግራየ ህዝብ ፍርሀቱን ጥሎ በተባበረ አሥተሣሠብ ከተነሣ በቀላሉ ለሥርአቱ ለድርድር ሊያንበረክከው ይችላል:: የዝብ የተባበረ ተቃውሞ ከሣዬ ወጤቱ በኦሮሞ ሀዝብ በተጨባጭ እየታዬ ነው:: ሥለዚህ የመቀሌ ተቃውሞ እጅግ ጥሩ ሙከራ አደርጌ እመለከተው አለሁ:: ለዚህ የመብት ጥያቄ ለማፈን የመንግሥት መሪዎች የቀበሌ ተላላኪዎች ካድሬዎች ድህንነቶች በቡዙ አካባቢዎች ተሠብሥበው ሢመክሩ ወለዋል::

ሢመክሩበት የዋሉ አጀንዳም: በየቤታቸው እየሄዱ በቤተሠብ በጓደኝነት በዘመድ ጎረቤት በመሥበክ መከፋፈል ወይ በማሥሥፈራራት ታርጋ ትቀማላችሁ በከተማው አገር አቋራጭ ሚኒ ባሥ አሠማርተን አገልግሎት እንሸፍናለን በሚል ለባለንብረቶች ሥጋት መፍጠር አለብን ብለው እንደወሠኑ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል: : ዋናው ሥጋታቸው ለነዚህ ጥቂት አድሞኞች ከተንበረከክን በትግራይ ቡዙ የዳፈነ የተቃውሞ ረመጥ ሥላለ በቸለልተኜት ከተመለከትነው የሚመጣው ጠንቅ አንቆጣጠረውም ሥለሆነ በፍጥነት ሁኔታውን እንቆጣጠረው ብለው እንደወሠኑ ምነጮች ጠቁመዋል::

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.