የሐገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የፓትርያርኩን ትዕዛዝ አልተቀበሉም

yemane-zemenfes

(ሳተናው)  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ለልጃቸው ሕክምና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑላቸውን የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም 10 የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን ከሥራና ከደሞዝ ካገዱ በኋላ  ፓትርያርኩ እግዱን ሽሪያለሁ ቢሉም ሰዎቹ ወደመደበኛ ስራቸው መመለስ አልቻሉም፡፡

ሊቀ ማዕምራን ለታማሚ ልጄ  ማሳከሚያ በማለት ገንዘብ በማሠባሰብ ላይ እንደነበሩ መነገሩና ሰነዶችም ለእይታ መቅረባቸው አይዘነጋም፡፡ ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ገዳም ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ እንዲሰጣቸው ቢወስንም፤ የገዳሙ ሒሳብ ሹም ክፍያውን አልፈጽምም በማለታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የቀድሞው የኢቴቪ የትግርኛ ፕሮግራም ዜና አንባቢ መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ የገዳሙን አስተዳደር በመሰብሰብ  ከስራና ከደሞዝ ያሰናበቷቸው መሆኑን አሳውቀዋቸዋል፡፡

የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት እግዱ ከተላለፈባቸው በኋላ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት በማምራት የተፈጠረውን ነገር ለፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ በማስረዳት ወደስራቸው እንዲመለሱ ያደርጉ ዘንድ ይማጸናሉ፡፡አቤቱታውን ያዳመጡት ፓትርያርኩ፤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጁን እገዳ በማንሳት የገዳሙ የአስተዳደር ኮሚቴ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በላኩት ደብዳቤ አስታውቀው ነበር፡፡

የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት በተከታዩ ቀን ወደመደበኛ ስራቸው ለመመለስ ወደገዳሙ ቢያመሩም መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በሀዘን ወደመኖሪያ ቤቶቻቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.