ሚንስትሯ በፓርላማው ከእንቅልፋቸው ተቀሰቀሱ

ማል

‹‹የምንከፍላችሁ እንድትተኙ፣ አይደለም እዚህ አትተኙ››

(ሳተናው) አፍሪካ ፓርላማ የእያንዳንዱ ዕለት ውሎ በአባላቱ መካከል  ዱላ ቀረሽ ፍጭት የሚደረግበት ከፍና ዝቅ ተደራርገው የሚሰዳደቡበት፣ወረቀቶች ተወርውረው በገላጋዩች አልያም በዋናነት የኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ አባላት በጸጥታ ሰራተኞች ተገፍተው የሚባረሩበት መድረክ ነው፡፡

የየዕለቱን የፓርላማ ውሎ ደቡብ አፍሪካዊያን በጉጉት የሚጠብቁት ተከታታይ ልብ አንጠልጣይ ፊልማቸው ነው፡፡ተቃዋሚዎች የገዢውን ፓርቲ ኤኤንሲ አመራሮችና በዋናነትም ጃኮብ ዙማን የሚያብጠለጥሉበትና የተሻለ አማራጭ እንዳላቸው የሚያሳዩበት የትወና ሰዓታቸው ነው፡፡

በትናንትናው ዕለት የፓርላማ የውይይት አጀንዳ ደግሞ በቅርቡ በመንግስት ወጪ አፓርታማቸውን መገንባታቸውን በመግለጽ ይቅርታ በይፋ ስለጠየቁት ጃኮብ ዙማ ነበር፡፡በቀለጠው ክርክር መካከል ግን የኤኤንሲ አባሏና የፖሊስ ሚንስትሯ ማይቴ ኒኮና ማሻባኔ እንቅልፏን እየለጠጠች ነበር፡፡

የተቃዋሚው ፓርቲ አባልና የፓርላማው ተወካይ የሆኑት ቡዬሴኒ ኒዶሎዚ ሚንስትሯን በዝምታ ሊያልፏት አልወደዱም እናም የድምጽ መነጋገሪያውን በመያዝ ‹‹የተከበሩ አፈ ጉባኤ ሚንስትሯ እንቅልፏን እየለጠጠች ነው፡፡ምን እየተካሄደ እንደሆነ አይገባኝም፡፡እዚህ እንድትተኛ ደሞዝ አንከፍላትም፡፡በንቃት የምንለውን እንድትሰማና አስተያየት እንድትሰጥ እንጂ እንድትተኛ አንከፍላትም››በማለት ግሳጼ አስተላልፉባታል፡፡

ሚንስትሯ ከእንቅልፏ ተነስታ ጣቶቿን ወደ ነቃፊዋ በመቀሰር ስትዝት የተስተዋለች ቢሆንም የፓርላማው አፈ ጉባኤ ቤቱን ስነ ስርዓት ለማስያዝ ‹‹አንቺም አንተም ዝም በይ(ል) ማለታቸውን ከተለቀቀው የቪዲዮ ማስረጃ ማየት ይቻላል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=c5IQ5UVgFeE

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.