ሳዑዲ አረቢያና ግብጽ በቀይ ባህር ድልድይ ለመገንባት ተፈራረሙ

red

(ሳተናው) የሳዑዲው ንጉስ ሳልማን ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ‹‹ታሪካዊ እርምጃ ››ያሉለትን አፍሪካንና ኢስያን የሚያገናኝ ድልድይ በቀይ ባህር ላይ ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈጸማቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ንጉሱ የስምምነቱ አካል የሆነው በቀይ ባህር ላይ የሚገነባው ድልድይ በዋናነት ሳዑዲንና ግብጽን ያገናኛል፡፡

በግብጽ የሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት በተጀመረ በሁለተኛ ቀኑ በአገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቭዥን በተላለፈ ስነ ስርዓት ንግግር ያደረጉት ንጉሱ ከግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ድልድዩን በተመለከተ ተነጋግረው መግባባት ላይ በመድረሳቸው ደስታ እንደተሰማቸው የጠቀሱ ሲሆን በዕለቱም የግብጽና የሳዑዲ ባለስልጣናት የንግድ ስምምነት ለመፈጸም በሚያስችሏቸው መግባባቶች ላይ በመድረሳቸው መፈራረማቸው ታውቋል፡፡

‹‹ከወንድሜ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ተስማምቻለሁ፡፡ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውም ድልድይ እውን ይሆናል፡፡የድልድዩ መገንባትም ሁለቱን አገራት በብዙ መንገዶች ተጠቃሚዎች ያደርጋቸዋል››ብለዋል፡፡

ድልድዩ በባህሩ የትኛው አካባቢ እንደሚገነባ ባይነገርም በግብጹ ናቢቅና በሳዑዲው ራስ አልሼኪ አቅራቢያ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

የግበጹ ፕሬዘዳንት በበኩላቸው የድልድዩ ስያሜ ንጉስ ሳልማን ቢን አበደል አዚዝ እንደሚሆን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.