የቀድሞዋ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚንስትር ‹‹የዘንድሮው ድርቅ የመጨረሻው አይደለም››ይላሉ

Invigning av Öresundshuset i Visby under politikerveckan, söndag 29 juni 2014. Foto: News Øresund - Johan Wessman © News Øresund(CC BY 3.0)   Detta verk av News Øresund är licensierat under en Creative Commons Erkännande 3.0 Unported-licens (CC BY 3.0). Bilden får fritt publiceras under förutsättning att källa anges (Foto: News Øresund + fotografnamn). The picture can be used freely under the prerequisite that the source is given . News Øresund, Malmö, Sweden. www.newsoresund.org. News Øresund är en oberoende regional nyhetsbyrå som ingår i projektet Øresund Media Platform som drivs av Øresundsinstituttet i partnerskap med Lunds universitet och Roskilde Universitet och med delfinansiering från EU (Interreg IV A Öresund) och 14 regionala; icke kommersiella aktörer.

(ሳተናው) የአየር ጸባይ ለውጡ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ቀውስ በመፍጠሩ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት አልሚ ምግብ በማጣት ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚገኝ ሴቭ ዘ ችልድረን አስታውቋል፡፡

የቀድሞዋ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚንስትር ሄሌ ቶርኒንግ ሽሚዲት ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን ችግር በመቋቋም እንድታልፍና በቀጣይም የድርቅ አዙሪት ውስጥ እንዳትሽከረከር ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

ከክላይሜት ሆም ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት በኢትዮጵያ በመገኘት በድርቁ የተጎዱትን አካባቢዎች የጎበኙት ሄሌ ‹‹በእርግጠኝነት ይህ ችግር በቀጣይም ከዚህ በላይ በከፋ መልኩ እንደሚከሰት መናገር እችላለሁ፡፡ይህ ድርቅ ለኢትዮጵያ የመጨረሻዋ እንደሚሆን ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም፡፡ ይህ አጋጣሚ ወይም መጥፎ እድል ስለመሆኑም አላምንም፡፡ድርቁ ባለፉት 50 ዓመታት ከታዩት መጥፎው ነው››ብለዋል፡፡

 

ሴቭ ዘ ችልድረን ባወጣው ሪፖርት 30 ሚልዩን ኢትዮጵያዊያን በድርቁ ምክንያት ለርሃብ እንደሚጋለጡ መጠበቁን በመግለጽ 6 ሚልዩን ህጻናት የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው በመሆኑ አፋጣኝ እርዳታ ያሻቸዋል ብሏል፡፡100 የእርዳታ ማዕከሎችን በኢትዮጵያ ማዘጋጀቱን የገለጸው ድርጅቱ ዝናብ በአገሪቱ በተወሰኑ ቦታዎች መጣል መጀመሩ እፎይታ መፍጠሩንም አስታውቋል፡፡

ዴንማርክን ከ2003 እስከ 2007 በጠቅላይ ሚንስትርነት የመሩት ሄሌ ድርቁን ለመቋቋም እቅድ የሚያወጡ አካላት የረዥም ጊዜ እቅድ እንዲነድፉ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ከድቁ በኋላ ምን መደረግ እንደሚኖርበት በፍጥነት ማሰብ ይኖርብናል፡፡፡በአጭርና ረዥም ጊዜ ውስጥ ልንወስዳቸው የሚገቡን እርምጃዎችን ከወዲሁ ማስመር ይጠበቅብናል፡፡የእኔ ጭንቀት የህዝቡ መጻኤ ጊዜ ጭምር ነው››ይላሉ፡፡

ወይዘሮዋ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት በሶሪያና በሜዲትራኒያን አካባቢ በመያዙ የእርዳታ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የሚስፈልጋትን ያህል ድጋፍ ለማሰባሰብ መቸገራቸውንም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ሴቭ ዘ ችልድረን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.