የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ቢሮ ትናንት ታሸገ – ሳተናው

Addis adamas(ሳተናው) በአድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ.የተ.የግ.ማ  ታኅሣሥ 29 ቀን 1992 ዓ.ም የተመሰረተውና እስካሁን ድረስ በየሳምንቱ ቅዳሜ እየታተመ ለአንባቢያኑ ሲደርስ የቆየው አንጋፋው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ለዓመታት የተጠቀመበት ቢሮው በልማት ምክንያት እንዲፈርስ በመወሰኑና የጋዜጣው ባለቤቶች ቢሮውን እንዲለቁ በተነገራቸው ወቅት ባለመልቀቃቸው ትናንት ማለዳ በቀበሌ ሰራተኞች የድርጅቱ ንብረት ሳይወጣ መታሸጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ቢሮ ካዛንችስ፤ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር ገባ ብሎ፣ ከጤና ጣቢያው ጀርባ በቂርቆስ ክ/ከ ቀበሌ 31 ፤ የቤት ቁ.376 ውስጥ ይገኝ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጋዜጣው ባልደረቦች በሌላ ቢሮ ውስጥ መደበኛ ስራቸውን በማከናወን ላይ እንደሚገኙም የሳተናው ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

የጋዜጣው ባለቤቶች ቤቱን ከመልቀቃችን በፊት የ90 ቀናት ማስጠንቀቂያ ሊሰጠን ይገባል በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ቢታወቅም የዘጠኝ ቀናት የመልቀቂያ ጊዜ ሰጠ የተባለው የቂርቆስ ክ/ከ ቀበሌ በኃይል ቢሮውን ማሸጉ ተነግሯል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.