ሰበር ዜና: አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ለትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ እራስ ምታት ሆኗል

በልኡል አለም

Andargachew 1 - satenaw
አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ

የተከበሩት የቀድሞ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ለወያኔ በግፍ ተላለፈዉ ሲሰጡ የእንግሊዝ የደህንነት አካላት ያዉቁ እነደነበር እና የየመን የጸጥታ ሐይሎች እንዲሁም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በመተባበር እገታዉን እንዳካሄዱት ዛሬ ከብሔራዊ መረጃ ምንጭ ተገኝቷል።

የእንግሊዝ ከፍተኛ የደህንነት አባላትን ጨምሮ አጣብቂኝ ዉስጥ የከተቱት አንዳርጋቸዉ ጽጌ በአምነስቲ ኢንተርናሽናልና በሌሎች ሁለት ከፍተኛ ተደማጭነት ባላቸዉ የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲሁም በወላጅ አባታቸዉ የሚጎበኙ ሲሆን የተለያዩ የወያኔን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዲስኩር ያዘሉ መጽሐፎች፣ እና መጽሄቶች በተለይም የክቡሩን ታጋይ ሞራል በሚነካ መልኩ አንዳንድ አልባሌ ጽሁፎችን ያካተቱ መጣጥፎችም ሆን ተብለዉ እንዲሰጡት ቢደረግም በጀግናዉ አንዳርጋቸዉ ላይ እየታየ ያለዉ አልበገር ባይነት በወያኔያዊያን ላይ የበላይነቱን ይዟል።

በተልይም የደህንነት ቢሮዉ ሚስጥራዊና ልዩ ስብሰባ ያካሔደ ሲሆን የእንግሊዝ ባለስልጣናት እራሳቸዉን ከተጠያቂነት ባሸሸ መልኩ በተገላቢጦሹ ታጋይ አንዳርጋቸዉን እንድንፈታ እያስገደዱን ነዉ። “ሰባዊ መብት ጥሰቱ እስካልቆመና አንዳርጋቸዉ ጽጌ ካልተፈታ ወይም አስቸኳይ የሆነ የአቋም ለዉጥ በኢትዮጵያ በኩል እስካልተደረገ ድረስ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚሰረዝ ማሳስጠንቀቂያ አዘል ትእዛዝ ተሰጥቶናል” በሚል አጀንዳ ተንተርሶ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ጭንቅ ዉስጥ ገብቷል።
እንዳይለቁት እሳት እንዳይዙት መአት!!! ይሏል ይህ ነዉ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.