እድገት ብሎ ውሸት (ዶር አክሎግ ቢራራ)

እድገት ብሎ ውሸት ዶር አክሎግ ቢራራ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚታወቀው ከላይ ወደታች በሆነ የእዝና የቁጥጥር መርሆ ነው”

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

አገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እንዳሉባት ከላይ ያቀርብኳቸው ጥቅሶች ያካትቱታል። ከሁሉም በላይ “የአአምሮና የመንፈስ ችግር” ስር ሰዶ ሕዝቡን ሽባ ማድረጉ ለችግሮቻችን ሰው ሰራሽ የሆነ ማህበረሰባዊ ውድመት መሰረት ሆኗል። በፖለቲካው፤ በአገዛዙ፤ በማህበረሰባዊ አስተሳሰቡና አመለካከቱ፤ በኃይማኖቱና በኢኮኖሚው፤ በውጭ ግንኙነቱና ሌላው ጠለቅ ብሎ ሲታይ ጠባብ ዘረኛነትና ጎሰኛነት ሕዝቡን ለእርስ በርስ ግጭት፤ ለድህነትና ለስደት፤ አገሪቱን ለመከፋፈልና ለጥፋት ዳርጓቸዋል። የዚህ ሃተታ መሰረታዊ ሃሳብ ዘረኛነትና ጠባብ ጎሰኛነት መፍትሄ ካላገኙ አደጋው እየተባባሰ ይሄዳል የሚል ነው። የፈለገውን ያህል የአስተዳደር ብልሺትና በደል፤ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ስርዓታዊ ሆነዋል የሚል ትችት በያቅጣጫው ቢሰነዘርና የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ይህን ቢያምኑም የችግሩን መንስኤ፤ ማለትም፤ ጠባብ ዘረኛነትንና ጎሰኛነትን ለመተቸትና ለመፍታት ካልቻሉ አፋኙ፤ አግላዩ፤ ኪራይ ሰብሳቢውና ሙሰኛው ስርዓት ይቀጥላል። ድርብ አሃዝ ተብሎ የሚለፈፈው የእድገት መጠን ይቀንሳል። ለሰብአዊ አገልግሎትም ሆነ ለልማት የሚሰጠው ግዙፍ የውጭ እርዳታ ችግሩን አይፈታውም። በሌሎች አገሮች የሆነውን መሰረት አድርገን አግባብ ያለው መልስ ለመስጠት ብንሞክር ጥገኝነት ሁኔታውን ያባብሰዋል። ተከታታይ የድርቅ ረሃብ ምሳሌ ነው።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.