የመርሳን ጥንዶች ምን ገደላቸው? (ሳተናው)

balena mist

(ሳተናው) ጥንዶቹ ትዳር መስርተው ጉልቻ የመሰረቱ አልነበሩም፡፡በአፍላ ፍቅር ላይ የነበሩት ጥንዶች ታሪካዊቷን ዕለት 08/08/2008ን በአንድነት ለማሳለፍ በመርሳ ከሚገኙ ሆቴሎች በአንዱ አልጋ ይይዛሉ፡፡

የሆቴሉ አልጋ ክፍል አስተናጋጆች በማግስቱ ተከራዩቹ ጥንዶች ክፍሉን እንዲለቁ ለመንገር የክፍሉን በር ደጋግመው ያንኳኳሉ ፡፡ከውስጥ ምላሽ በመጥፋቱም ለማንኛውም ፖሊስ ጠርተው በሩ በኃይል ተገንጥሎ ይከፈታል፡፡

አልጋው ላይ ተቃቅፈው የነበሩት ወጣቶች እስከወዲያኛው አሸልበዋል፡፡ምንም አይነት ደም አልፈሰሳቸውም፣መስኮቶቹ ግጥም ተደርገው እንደተዘጉ ከመሆናቸውም በላይ የሆቴሉ በርም የተከፈተው ተገንጥሎ ነው፡፡መርሳ የአስከሬን ምርመራ ማዕከል ያልነበራት በመሆኑም የጥንዶቹ አስከሬን ወደ መቀሌ ይላካል፡፡

ወጣቶቹ አረፋ በአፋቸው ደፍቀው እንደነበር በማህበራዊ ገጾች ከተለቀቀው ምስላቸው መረዳት ይቻላል፡፡የመኝታ ክፍሉ ከምግብ ማብሰያ ክፍል ጋር የተያያዘ ከሆነና የከሰል ጭስ ወደውስጥ የሚገባ ከሆነ መንስኤ ሊሆን ይችላል ከሚሉ መላ ምቶች አንስቶ ሆን ተብሎ በጋዝ እንዲታፈኑ ተደርገው ይሆናል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችም አልጠፉም፡፡

ግድያ ተፈጽሞባቸው ከሆነም ረቀቅ ያለ ዘዴን ገዳዩቻቸው ለመጠቀማቸው የአሟሟታቸው ሁኔታ ያስረዳል፡፡እንዲህ አይነት ወንጀለኛን በምርመራ ለማግኘት ደግሞ ‹‹በመግረፍና በማሰቃየት ለማሳመን በሚጥሩ ፖሊሶች አቅም የሚደረስበት ስለመሆኑ ብዙዎች ጥርጣሬ አላቸው››፡፡

አሳዛኙ ነገር የጥንዶቹ ቤተሰቦች መቀሌ አስከሬኑን አስመርምረው ወደ መርሳ ሲመለሱ ቆቦ ላይ የተሳፈሩባት መኪና ከተሳቢ ጋር በመላተሟ የተወሰኑት ወዲያውኑ ህይወታቸውን ሲያጡ ቀሪዎቹ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.