ህዝብ አይዳናገርም ከእናንተ በልጦ ተራምዷል!! (ከአሥገደ ገብረሥላሤ መቀሌ)

ሠወሥተኛ ወያኔና  የህወሓት ተላላኪ ካድሬዎች
የሥም ማጥፋት ዘመቻ ተያይዘውቷል

Asgedeእነዚህ ጸረዲሞክራሢ መሆናቸውና ፖለቲካዊ አቅማቸው የላሸቀና ከሥድብ ውጭ  ልዩነትን በሀሣብ ማሥረዳት ባህሪያቸው የማይፍቅድላቸው መሆኑ እያረጋገጡ ይገኛሉ:: በሌላ በኩል በጠባብነት ሥሜት በመነሣት  የማይናቅ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወለጆች የሆኑ የድህረገጽ ጸሓፊዎች ሥለ በኢትዮጱያ ያለው ነባራዊ ሁኔታና  የህወሓት ኢህአደግ አፈናና ጸረ ዲሞክራሢ ተግባራቸው: የሀገራችን ህዝቦች ማለት በትግራይ: በኣማራ:በኦሮሞ:

በጋንቤላ በቅማንት በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ችግሮችና መፍትሂዎች በሚዘግቡበት በአማራ: በሸዋዎች ለመወደድ ብለው የሚጽፉት  ነው በማለት  ያቋሹሿሉ::
እነዚህ ሠዎች አማራ ሽዋዊ ሥሉ የሽዋ ህዝብ የአማራ  ህዝብ  የአገው የኦሮሞ ህዝብ  እኮ  ልክ አንደ ትግራይ ህዝብ እየተጎዳ ነው ያለ:   ለምን እንዲጠሉ ይደረጋል?? ይህ የሚያሣዬን ትግራይን ከእናት አገሯ ኢትዮጱያ ለመገንጠል ሆን ተብሎ ይደረግ ያለ ሤራ ነው::

እነዚህ ሠዎች የትግራይ  ህዝብና መሬታ ለመገንጠል እንደማይችሉ ግን ህዝብ ድሮም አሁንም  የኢትዮጱያ መሠረት መሆኑ አረጋግጦት ያደረ መሆኑ  አበጥረው ያውቃሉ:: ሌሎች ኢትዮጱያውያንም  ይህን ሀቅ አይክዱም እነዚህ ሠዎች ዋናው ችግራቸው ከእንግዲህ ወዲህ የትግራይ ህዝብ የነሡ መደበቂያ እንደማይሆን አለመገንዘባቸው  ነው  ችግራቸው::

አንድ አሥቅእኝ ነገር ግን ልነገራችሁ::እነዚህ ፉጡራን ቁምነገር እንደሌላቸው  ልትገነዘቡልኝ   እምፈልገው አንድ አሠወሥተኛ ወያኔ ብለው ከሚያደናግሩ አነዱ  እኔ በማጋለጤ የሠጠኝ አሥተያየት ቢኖር: አንተ መንቻካ አሮጌ አታርፍም : አንተሽዋዊ የሚሉ ቃላቶች ሠነዘረ::
ይህ አገላለጽ  ከላይ እንደገለጽኩት የወረደ አነጋገር ነው

ይህ ግለሠው አለማወቁ ነው እንጅ  አንደኛ እድሜ ጸጋ መሆኑ ማመን አለበት::  ሁለተኛ የሚያሥተላልፈው መልእክት  ነው መሥፈርት መሆን ያለበት::እኔ አሮጌ ቢለኝ ደሥ ይለኛል  እሡ ግን እንደ ሥድብ መቁጠሩ  ከዛ በላይ አቅም የለውምና::  አቅም በሚመለከት ቢሆን በ67  አመት እሜየን ለዚ ግለሠው ያለጥርጥ እበልጠው አለሁ::የኔ አሰላለፍም    ከሠወሥተኛ  ወያኔ ሣይሆን  ከሀቀኛ ለውጥ  ፈላጊዎች መሆኔ ማወቅ ይኖርበታል::

ሌላ እች ትግራይ ትግራይ የምትሏት 100 000በላይ ልጆቻ ሠውታ  ከ126000በላይ ለጆቻ አካል ጉዳተኛች አድርጋ ይህ ከሸአብያ ጦርነት ሣይጨር  ምንተጠቀመች ተጠቃሚዎች እኮ አሁን ያሉ ቁነጮዎችና  ዘርመንዝራቸውና  አደርባይ ካድሬና ሸሪኮቹ ናቸው:: በመሆኑ ይህህዝብ የናንተ  ተገዥ ሊሆን አ  ፍጹም አይሆንም::  የኢትዮጱያ ህዝብ በቃ የአንድነት  ጎደና ብሩህ ተሥፋ ሁኖለታል::  ድሮም የተግራይ  ህዝብ  ብጅታ አልነበረውም::   እናንተ ግን በኦሮሞ  ይህ የሚያህሉ የተግራይ ተወላጆች ተገድለዋል ሀብታቸው ተወርሠዋል : በአማራ ተገድለዋል ተዘርፈዋል : በጋንቤላም እንደዚሁ አልቀዋለ:: ሥለሆነ የትገራይ ህዝብ በየሄደበት ይደራጅ  ህወሓት ከተዳከመ  ትግሬ የሚባል በዝህች መሬት አይኖራትም በማለተ በሀዝብ ውሥጥ ሥጋት ለመፍጠር በመላው  ትግራይ መርዝ ትረጫላቹሁ :  ይህ መርዛችሁ መርጨቱ ለዚህ ህዝብ አይጠቅምም::  ለናንተም መደበቅያ አይሆንም::

ይልቁን የማይጠገነው ህወሓት ከመቃብር  ለማውጣት ከምትታክቱ ሁሉም ተግባራችሁ  በኢትዮጱያ  90ሚሊዮን ህዝብ መሥተዋት  አድርጋችሁ ፊታችሁ  ብትመለከቱት መልካም ነበር::

በመጨረሻ ለትግራይ ወጣቶች እማሥተላልፈው መልእክት እነዚህ በሥመ የትግራይ ህዝብ እየነገዱ እሚያደናግሩ ተቀጥያዎች ያራሙዱት ያሉ የመደናገር እንቅሥቃሤ በሀሣብ መከላከል ብቻ ሣይሆን  በሀሣብ ወደ ማጥቃት በመሸጋገር   በሠላማዊ መንገድ መታገላቸው ያሻል::

ከአሥገደ ገብረሥላሤ መቀሌ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.