ሀዝብ ሣይንከባከቡ ውድቀት እንጅ ክብር የለም!!!!!!!(አሥገደ ገብረሥላሤ-መቀሌ)

12sd2

ለዜጎቹ  ሣይንከባከብ ለፓለቱካዊ ፎጆታ  ትርፍ  ተብሎ በአለም  አቀፍ  መድረክ  ልታይ ልታይ  ፋይዳው ምንድነው?  ማጭበርበሩሥ ለምን ?
የኢህአደግ ሥርአት  የአጎራባች  አገሮች  ሥደተኞች  መጠልያ በመዘጋቸት ተቀብሎ አለም አቀፍ እርዳታ ጠይቆ  መንከባከቡ  የትምህርት  እድል ሥራ መሥጠቱ  የሠበአዊ ነት  ተግባር  ከመሆን  አልፎ  ለሠው ልጅ ክብርና  ፍቅርን ተብሎ የሚደረግ ያለ መሥሎ ይታያል::
ኢህአደግ ግን  ለውጭ ሠወች ከሚሠጠው እንክብካቤ  ህዝባዊ ፍቅር   መተሣሠብ  አንጼር  ሢታይ ለዜጎቹ  ርህራሄ  እንክብካቤ , ፍቅርና መቆርቆር አያሣይም ?በአሁኑ  ወቅት በኢትዮጱያ ዙሪያ ወይ 360 ዲግሪ አሚያዋሡኑት አገሮች  ተሠድዶው  በባህር  ሠጠሙ ታረዱ, ታሠሩ ወይ በእሡር ቤት ሞቱ,   ወዘተ የሚል መርዶ  በውጭ ሚዲያዎች  ተነግሮ  ወላጅ ዘመድ ጥቁር ልብሥ ለብሠው ሢታዩ ምንሆናችሁ  ሢባሉ ልጆቻችን በሥደት ተደገሉ ይላሉ :: የኛ መንግሥት ደግሞ የራሡ ችግር  እንደመፈተሽ ፈንታና እንደማዘን  ለታሠሩ ለሚሠቃዩ ዜጎቹ በመደራደር የዜጎቹ መብት እንዲከበር  እንደመጣር ፈንታ  እነዚህ የሚሞቱ የሚታረዱ ያሉ  ዜጎች   በአገራቸው ሠራ አጥተው ሣይሆን  በአቋራጭ ለማደግ ፈልገው ነው በማለት  ለህዝብና ለአለም  ያጭበረብራል:: ሀቁ ግን  በቅርብ ጊዜ ራሣቸው  እንደተናገሩት  በትግራይ 900   ወጣት በኦሮሞ ከ2.3  ሚሊዮን  በላይ ከአመራ ከጎንደር ክፍለሀገር በቻ  800 ወጣቶች ከ18 እሥከ 30 አመት እድድሜ ሥራ አጥ ወጣቶች አሉ ሢሉ ሠንብተዋል:: ይህ የሥራአጥ አሀዝ ግን እጅጉን አንሥተኛነው በሀገራችን ከ43 አመት እድሜ በታች ሥራ አጥ ነው :: ምክንያቱም ወጣት አርሦ አደር  መሬት የለውም:: የከተማም የተማረም ያልተማረም ሥራ የለውም:: የኮንሥትራክሽን  የተወሠነ ሠራተኛ  ይይዝ ነበር መነግሥት መሬት የመንግሥት ነው አንተህዝብ ጢሠኛ ነህ ብሎ የመሬት ባለቤትነቱ  ከነጠቀው በኋላ ዜጎች ቤት ሥለማይሠሩ የኮንሥትራክሽን  እንድሥትሪ ቆመዋል :: በመሆኑ በሁሉም መልኩ ወጣቱ ጨንቆት በገደና ወድቀዋል ::
ይህ ሥርአት መቸ ለተሠደዱ ዜጎች አለመቆርቆርና  አለመጣበቅ ብቻ  ባገር የቀረው ህዝብሥ መቸ ሠክኖና ተረጋግቶ ባገሩ መኖር ዋሥትና አገኘና ?በሠሜን ለረጅም ጊዜ በሸአብያ ሂወቱ ሀብቱ እየተወረረ ኖሮዋለ  የባሪያ አገዛዝም እየተመፈጸመት  ይገኛል:::: በምሥራቅ ሥዳን : በደቡብ ሡዳን በሥማል በጅቡቲ በከኒያ ጠረፎች በየቀኑ የሚገደሉ ዜጎች እጅጉን ቡዙ ናቸው:: በቅርብ ቀናት እኳን  ደማቸው ያልደረቀ  የጋንቤላ ወገኖች  እልቂት አይተናል  አለም ተናግሮለታል አሁንም ግድያ አላቋረጠም:: አሁን ደግሞ ዘግናኙ መርዶ 208 ዜጎቻችን አዲሥ መርዶ ባህር የበላቸው በውጭ ሚድያ  ተነግሮናል::
የኛ መንግሥት ግን  ባለፈው ጊዜ ይሁን የአሁኑ አደጋ የሚዲያ ሽፋን ሊሠጥሥ ይቅር  በደብቅ ደብቅ  ሊተለፍነው የሚፈልገው:: የአሁኑ የጋንቤላ ወገኖች ጅምላ ግድያ ለመግለጽ የተገደደውም  ድርጊቱ በውጭ ሚድያ  አፈትልኮ በመውጣቱ  እንዳይዋረድ ተገዶ የተናገረው ነው:: ሌላ ቀርቶ አገራዊ ሀዘንም እንዳይባል ተገዶ የጭንቀት ያወጀው ነው::
በገር ቤት ያለው ህዝብሥ ምን እየሆነ ነው ? በአሁኑ ወቅት እኮ ሥራ ያጣውም የሚሠራም ሙሁሩ አርሦ አደሩ ነጋዴው ባለሀብቱ  : ፖለቲከኛው : የሀይማኖት ተቃማት መቸ ሠክነውና ተረጋግተው እቺ የሀገራቸው መሬት  በነጻነት   በራሥን መተማመን  መቸ ረገጡዋትና:: አሁን እኮ እች ሀገር ጥቂት ማፊያዎች አንደኛ ዜጎች ሁነው  በምን አለብኝነት  እየቀጠቁጧት የሚወሩዋት  የሚሸጡዋት የሚለውጧት ሥትሆን: ሌላው ኢትየጱያዊ የሁለተኛ ዜጋ መብት እንኳን ተነፍጎት የሚኖርበት አገር ናት::
ታድያ ይህሥርአት  ሀገረችን የውጭ ሥደተኞች ተቀብላ ትንከባከባለች ታሥተምራለች እያለ ለንግድ በተጨማርም በሥደተኞች  ምክንያት ሀብትን ለመሠብሠብ ነው እንጅ  ይህ ሥርአት የሀዝብን ፍቅር ንሮት አይደለም::
የህዝብ ፍቅር ቢነረው ንሮ በዘንድሮ ድርቅ ዜጎች በቂ እርዳታ አጥተው ወደልመና ተሠማርተው የማያውቁ ወገኖች ህጻን ሽማግሌ አባቶችና እናቶች መጫቶች ሁለት ከዛበላይ ህጻናት አንጠልጥለው ለልመና ከተሞችን አጥለቅልቀዋል :: ለተቸገረ  ህዝብ የሚያዝንና ርህራሄ ካለው መጠልያ አድርጎ ወይ በየትውልድ  ቃያቸው አደርጎ  ለምን አይመግባየውም ? ለምን አያሥተምራቸውም? ለምን እንዲታከሙ አያደርግም ?
ታዱያ ይህ  ሥርአት  አታላይና አጭበርባሪ  ከማለት ምን አይነት ሥም ይሠጠዋል  ? መልሡ ለሁለም  ዜጋ ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.