ገብረክርስቶስ ደስታ እና እኛ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ይህ ምስል ታዋቂውን ሩሲያዊ ደራሴ ቶሎስቶይን ኣስታወሰኝ። ቶሎስቶይ የሰው ወንድ በደስታ ለመኖር መሬት እና ሴት ብቻ ነው የሚያስፈልገው ይላል ። ቶሎስቶይን ሰምተን ፥ ይህንን ሆሆታ ፥ ጋጋታ ፥ ዋይታ እና ትርምስ የባዛበትን አለም ለቀን ወደ እናት ሃገራችን ለመመልስ ብናስብ ፥ የሚገጥመን መሬት እና ሴት ሳይሆን የፌደራል ዱላና ፥ ከዱላው ጋ ግብግብ የገጠሙ መሬታቸው የተቀማ ጎበዞችን ነው ፥ እንሂድ እንግባ ብንል የሚተብቀን በመለስ ፋውንዴሽን እና ያንን ፋውንዴሽን በመቃወም በወደቁ ዜጎች ደም ከአረንጓዴነት ወደ ቀይ ምድርነት የተቀየረ መንደር ነው። ያኔ መሬት የውበት መገለጫ በሆነበት ዘመን ጋሽ ገብረክርስቶስ ሃገሩን እንዲህ ነበር የገለጠው

mendereሃገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
ሃገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ።
ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም
አይበርድም አይበርድም
ሃገሬ ጫካ ነው
እንስሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

ምናልባት ጋሽ ገብሬ ተመልሶ ቢመጣ

ሃገሬ ተራራው በከራስ ግብግብ የተደረመሰ
ጅረት እና ጫካው ፥ ለባዕድ ባለ ሃብት ተሽጦ ያለቀ
ጥንት የተጨረሰ
ውሸት ነው ባገሬ ጠሃይ ኣትወጣም
ክረምቱም ጅረቱን ውሃ ኣያጠጣም
ሃገሬ ሌጣ ነው ፥ እርቃኑን የቀረ
በድርቅ እና ረሃብ ሲታመስ የኖረ!

ከተማው ጫካ ነው ፥ ኣዳራሹ ጫካ
ጅብ እና ቀበሮ ፥ ዙፋን ላይ ቁጭ ብሎ
በነገስታት ቋንቋ
ንጉስ ነኝ እያለ ፥ ህዝብ ላይ ‘ሚያስካካ።

ሃገሬ በድን ነው ፥ ዲዳ ነው ሃገሬ
እዚያ ዝምታ ነው ፥ ጠጥታ ነው ዛሬ!

የሚል ይመስለኛል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.