የትግራይ ህዝብ የድሮ ስርአት ናፋቂ ተባለ!

ናትናኤል አስመላሽ

እንግዲህ ህወሓት የትግራይ ህዝብን የድሮ ስርአት ናፋቂ ማለት ጀምራለች። የእምባስነይቲ ህዝብ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ስላቀረበ፣ ህዝብ እንደ ህዝብ የድሮ ስርአት ናፋቂ ተብለዋል። በትግሉ ጊዜ ልጆቹን የገበረ ህዝብ ኣሁን የድሮ ስርአት ናፋቂ ተብለዋል። ይህ ማለት ደግሞ የትግራይ ህዝብ የታገለው ለራሱ መብት እና ነጻነት ሳይሆን ለህውሓት ባለስልጣናት ነው ማለት ነው።

ባለፈው ምርጫ መቶ በመቶ ኣሸንፈናል ያሉት ህውሓቶች አመት ሳይሞላቸው ህዝቡ ማመጽ ጀምረዋል። ህዝቡ ከዚህም ኣልፎ በሰልፉ ላይ ለሃያ ኣመታታ የጠየቅነው ጥያቄ ስላልተመለሰ ከወረዳ እስከ ፌደራል ያሉ ተወካዮቻችን ውክልናቸውን ኣስነስተናል ብለዋል። እንሆ ሁለት ሺ ስምንት ሳያልቅ መቶ ከመቶ ተመረጥኩ ያለው ህውሓት በኦሮምያ ብቻ ሳይሆን በትግራይም ተቃውሞ ደርሶበታል።

ህዝቡ ፓርላማ ያሉትን ወኪሎቻችን ኣይደሉም ብለዋል። ድንቄ ምርጫ መቶ በመቶ ተመርጠህ አመት ሳይሞላህ ህዝቡ መቶ በመቶ ኣንተ ላይ ሲያምጽ ይህ በአለማችን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ነው።በአለማችን ታሪክ ውስጥ ኣስራ ኣንድ በመቶ ለ አስራ ኣምስት ኣመታት ያደገነው እኛ ብቻ፣ በአለማችን ታሪክ ውስጥ ምርጫን መቶ በመቶ ኣሸንፈን ኣመት ሳይሞላን ህዝቡ መቶ በመቶ እኛ ላይ ሲያምጽ እዚቺው እኛ ጋ ብቻ ነው። ህውሃቶች የኦሮምያ፣የአማራንን የጋምቤላን፣የሶማልያን፣ ህዝብ ጨርሳ ጠመንጃዋን ወደ ትግራይ ህዝብ ኣዙራለች፣ መቀበርያዋ የተፈጠረችበት መሬት ላይ እንደሚሆን ኣያጠራጥርም።ደደቢት ተወልዳ ደደቢት የምትቀበር ህውሃት ብቻ ናት።በማን ቢባል በድሮ ስርአት ናፋቂው የትግራይ ህዝብ።

12q

13q

1E

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.