ዲሞክራቲክ አሊያንስ ‹‹አገራችን በተቀበረ ፈንጂ ላይ ቆማለች››

lamela

(ሳተናው) በደቡብ አፍሪካ የነጻነት ቀን የአገሪቱ ታላላቅ ፓርቲዎች ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የተሳተፈባቸውን ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች አድርገዋል፡፡ከወዲሁም በመጪው የነሐሴ ወር ለሚከናወነው ምርጫ ቁልፍ እርምጃ ተብሏል፡፡

አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ኤኤንሲ (አፍሪካን ናሽናል ኮንግረንስ)እና ተቃዋሚ ፓርቲው ዲሞክራቲክ አሊያንስ በሰልፎቹ ላይ የተለያዩ መልእክቶችን አንጸባርቀዋል፡፡

ኤኤንሲ በፕሬዘዳንቱ ጃኮብ ዙማ በኩል ለደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መልእክት በቀጣዩ ምርጫ ዋነኛ ተቀናቃኙን ዲሞክራቲክ አሊያንስን በዝረራ እንደሚረታ ፎክሯል፡፡

ዲሞክራቲክ አሊያንስ በበኩሉ ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው ጥቁር አፍሪካዊያን የአገሪቱ መሬት ባለቤቶች መሆን አለባቸው በማለት ለአመታት ሲያነሳው በቆየው ጥያቄ ዙሪያ ነበር ፡፡ፓርቲው ባሰራጨው መግለጫ ‹‹አገራችን በተቀበረ ፈንጂ ላይ ቆማለች፣ የደቡብ አፍሪካ ዴሞክራሲም ለመውደቅ ተቃርቧል፡፡የጥቁር አፍሪካዊያን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ካላገኘም ያገኘነው ነጻነት ሙሉ እንዳልሆነ ይቀራል››ብሏል፡፡

ምንጭ ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.