እንደምንዋላችሁ? በጠዋቱ ይሄን ሰማሁና ፈገግ አልኩ (አለምነህ ዋሴ)

ነገ ከወደቅንበት እንዳንነሳ ቸክሎ፣ከመሬት ጋር ስፍቶ ስለሚይዘን “ብሔራዊ ባቢሎን”የጩልቂት ከሚያሳዩ መቅሰፍቶች አንዲቷን አጅሬ ሰይፉ ፋንታሁን በሳይንሳዊ መንገድ አረጋግጦ አቅርቦልናል።ይህ ሰውዬ ከሺዎች አንዱ ነው።22 ቋንይቋ አቀላጥፌ እናገራለሁ ይላል።ችግሩ እሱ አይደለም።102ም ቢል ምን ችግር አለ?መሬት ምነው አንት ሰው ከበድከኝ አትል አፍ አውጥታ!ስንቱ የ”ታይታኒክ ካፒቴን”የሚፍለከለክባትም አይደለችምን?መቼም ታይታኒክን የማያውቅ የለም ብዬ ነው።

ያቺ “የማትሰምጠዋ!the unsinkable “ቆንጆ መርከብ!መቼም እሱን ፊልም ያላየ ይኖራል ብዬ አልገምትም።በውስጧ የነበረ ህልም ዕልም ህይወት! በእንደዛ ዐይነት የህልውና ችግሮች ሁሉ የተፈቱበትና ፍፁማዊ እውነት የተገለጠበት መርከብ ላይ ተሳፍረው ሲሄዱ “ወዴት ነው የምንሄደው?”ተብሎ ለምን ይጠየቃል?ወደየትስ መድረስ ለምን ያስፈልጋል? ይህ ሽርሽር በራሱ መተኪያ የሌለው አድራሻ አይሆንም ወይ?በርግጥ አንዳንድ የሶቅራጥስ ዐይነት “gadflies //ዝንቦች/’አረ ጎበዝ!ከፊትለፊት በረዶ እየተጋገረ ነው!ይቺን ወደ አዲሲቷ ዓለም ከተማ ኒውዮርክ የምትቀዝፍ “የመጪው ዘመን” spaceship ወድየትም የማያወጣ “Limbo!” ውስጥ ናት!ይላሉ።

ማን ቢሰማቸው?እና ታይትኒክ፣ይቺ ብረት የማገራትና መስታውት ያንቆጠቆጣት “crystal palace” ምን ትሁን ነው የሚሉት?22 ቋንቋ አቀላጥፈው የሚችሉና የተካኑ፣የአለም ሁነት በሚዳወርባት ውቢቱ የብስራት ከተማ ዱባይ አያሌ ባለ 110 ኮከብ ሆቴሎች በ”ቼፍ”ነት የሰራ፤በችሎታና በክህሎቱ ከመተማመኑ የተነሳ ራሱን ለፈተና ያቀረበ ሁነኛ ሰው በመምህርነት የተሳፈረባት ታይታኒክ መርከብ የማይገባትና ያልመረመረችው ምን የዓለም ሚስጥር ሊኖር ይችላል? እንደነዚህ ዓይነት የዓለምን መፍቻ ቁልፍ የያዙና የመርከቢቷን “high society” የሚመግቡ ቼፎች በሚገኙባት መርከብ ላይ ሳይሳፈሩ የቀሩ ዕድለ ቢሶች ናቸው።”ዛሬ’ኮ ነው የምንኖረው!”አለ አንድ ከፍተኛ የህይወት እመርታ ጎዳና ላይ በፍጥነት ሲነዳ ያገኘሁት ወዳጄ።

ነዳጅ ሊቀዳ ቆሞ ነው የተገናኘነው።በአንድ ምህዋር ላይ መሾር ካቆምን ቆይተናል።እሱ አሁን የጁፒተር ላይ ነው መሽቶ የሚነጋለት።እኔ በአጋጣሚ በመሬት አፈር ፍቅር የተለከፍኩ በመሆኔ ጁፒተርን የመሳፈሩንወርቃማ ዕድል ሳልጠቀምብት ቀርቻለሁ።ወዳጄ ትናንት እንዳልተኖረ፣ነገም እንደማይኖር ርግጠኛ በመሆን “ዛሬ’ኮ ነው የምንኖረው!” ማለቱ 22 ቋንቋዎች ለራሳቸው ማወቅ ብቻ ሳይሆን ትውልድ የሚያስተምሩና የሚቀርፁ ካሱዎችን audacity እንድቀበል ያደርጉኛል።

ከዚህ ቀደምም ልክ እንደሰይፉ በርካታና ጉምቱ “ካሱዎችን፣ዶ/ር ኢንጂነሮችን”የሚበረብር ትጉህ ሰምቼ አውቃለሁ።በዚህ የተነሳም “ምናልባት ያ የማንዴላ ቀብር ጊዜ መስማት ለተሳናቸው ያስተረጎመው የምልክት ቋንቋ ኤክስፐርት ‘የኛ ሰው’ ይሆን’ዴ ብዬ አስባለሁ።ወዳጄ “ዛሬ እኮ ነው የምንኖረው!”ሲል ፈረንጅ እንደሚለው “Tomorrow is here”ማለቱ ወይስ አንደኛውን “ነገ አይደርስም፤ነገ የለም”ማለቱ ነው?አረ ያስተርጓሚ ያለህ!የሚያሰኝቢሆንም ደግነቱ ልበ ሙሉው ካሱ አጠገባችን አለ።”ትሬቼንቶ ቭራቲኮ አቬሬ ኡኖ ግራም ፉርቶና!”እኔም ጣሊያንኛ እንደምችል ለመግለፅ ፈልጌ ነው።ለምን ትስቃላችሁ?ለኔ ብቻ ሲሆነው’ዴ የሚቆነስራችሁ?…

Video by Seifu on EBS

22 language