ታጋይ ይወድቃል፥ ታጋይ ይነሳል!

13124453_10154767645610744_6960868544678572551_nብለነው ብለነው ካልሆነ ነገሩ፥
እኛም አውሬ እንሁን እናንተም አድኑን፥
======================
እነዚህ ወጣቶች፣ ዓባይ ዘውዱ፥ ዓግባው ሰጠኝ፥ ዓንጋው ተገኝ፥ እና አስቴር ስዩም ይባላሉ፥ የሚኖሩበት አካባቢ ወደ ትግራይ ከተከለሉት የጎንደር መሬትና ለሱዳን በተሰጠው ድንበር ላይ በመሆኑ፥ ሕወሓት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በሕዝቡ ላይ ክፉኛ ጫና ሲያደርግበት፥ ግፍን ዓይቶ እንዳላየ ማለፍ ያልቻሉ የሰሜን አንበሶች ናቸው፥
ወጣቶቹ በጎንደር ምዕራብ ዓርማጭሆ ዓካባቢ የሚፈጸመውን ግፍና ዓገራዊ በደል ወደ አደባባይ በማውጣት የወያኔን አፈና፣ ግድያውን፣ መሬት ዘረፋውን፣ ማሳደዱን፣ መከራና ግፉን ሲያጋልጡ የኖሩ ወጣት ፖለቲከኞች መሆናቸውን እናስታውሳለን።
በሰሜን ጎንደር የሰቲት ሁመራ፣ የዳንሻና የአብደራፊ ተወላጆች የአብራሃጅራ የምዕራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች ዓባይ ዘውዱ፥ ዓንጋው ተገኝ፥ አስቴር ስዩም እና አግባው ሰጠኝ፥ ትምህርታቸውን በዩኒቨሪስቲ ደረጃ ዓጠናቀው የአስተዳደር፥ እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሲሆኑ አስቴር ስዩም በኬምስትሪ ማስትሬት ዲግሪ ያላት ወጣት ነች።

በሸንጎ ሲናገሩ የሚደመጡትንና መርተው ሲወጡ ዓዕላፍ የሚያስከትሉ የአገር ዓውራዎችን በጥይት በመግደል፥ በተባ ብዕርና በዓንደበታቸው የሚሞግቱ ልሂቃንን በወህኒ ቤት በማጎር፥ ቀሪውን በማፍለስ፥ ጎንደርን የትግራይ ለማድረግ በአርማጭሆ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ እየደረሰ ያለ ግፍና መከራ ከልክ እያለፈ ነው፥ የትግሬ ወያኔዎች ብድራቱንም ዓይችሉትም፥

አንጋው ተገኝ እና አባይ ዘውዱ፥ እኛ የታሰርነው፥ መብታችን ጠይቀን፥ የተበላሸውን የመንግስት አስተዳደር ተቃውመን ነው፥ ከዚህ በላይም ቢመጣ ለመቀበል ዝግጁ ነን፥ ይልቅስ ማዳበሪያ በግዳጅ አንወስድም ብለው ስለታሰሩት ገበሬዎች ግድ ይለናል ያሉ የገበሬ ልጆች ናቸው፥

አስቴር ስዩም ተምሬ ለሃገሬና ለሕዝቤ እጠቅማለሁ፥ ሳይማሩ ያስተማሩኝን ወገኖቸን ዓግዛለሁ በሚል ከፍተኛ ዓላማ የምትራመድ ተስፈኛ ወጣት ነበረች፥
የልጅ እናት ከመሆኗ ተጨማሪ እየሰራች ተምራ በዖርጋኒክ ኬሚስትሪ ማስትሬት ዲግሪ ስትይዝ፥ መጭውን ዘመን በዓዲስ ሕይወት እቀጥላለሁ እንጂ ከትምህርት ምረቃ በኋላ ማዕከላዊ የማሰቃያ ቤት እገኛለሁ ብላ ዓልገመተችም ነበር፥

የትግራይ ነጻዓውጭ ድርጅት ሕወሓት፥ እነ አባይ እና አስቴርን ወደ ማጎሪያና፥ የማሰቃያ ቤት ቢያስገባቸውም አፈናውና በደሉ እስከቀጠለ ድረስ በሰሜን ጎንደር በምእራብ አርማጭሆ ፣ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ምድር አያሌ አባዮች ይወለዳሉ፥ ብዙ አስቴሮች ይፈልቃሉ።

Source -Gondar Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.