ፖሊስ በኤርሚያስ አመልጋ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት

Access

ቤተሰቦቻቸው ለዋስትና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አሲይዘዋል

(ሳተናው) ኤርሚያስ አመልጋ ለተጨማሪ ስምንት ቀናቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ቤተሰቦቻቸው ፖሊስ ኤርሚያስን ለምን በዋስትና እንዳልለቀቃቸው ለፍርድ ቤት የሚያቀርበውን ምክንያት ሲጠባበቁ ፖሊስ አዲስ ክስ ይዞ መምጣቱ ታውቋል፡፡

ኤርሚያስን በመመርመር ላይ የሚገኘው ፖሊስ በግለሰቡ ስም የነበረን አንድ አይሱዙ መኪና ከሶስተኛ ወገን ማግኘቱ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱን እንዲጠይቅ አድርጎታል፡፡ፍርድ ቤቱም በፖሊስ የቀረበለትን የምርመራ ጊዜ በመፍቀዱ ኤርሚያስ ቀደም ብሎ የተፈቀደላቸው ዋስትና ተግባራዊ አይሆንላቸውም፡፡ኤርሚያስ መኪናውን በማስመልከት ለፍርድ ቤቱ መኪናውን በህጋዊ መንገድ ያላስለታለፍኩ በመሆኑ ተጠያቂ ልሆን አልችልም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

115 ቀናት በፖሊስ ጣቢያ ያሳለፉት ኤርሚያስ አሁን ለቀረበባቸው ክስ በቀጣይ ዋስትና ቢጠይቁ እስከ 30.000 ብር ለዋስትና ሊጠየቁ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ኤርሚያስ ሲያቀርቧቸው የቆዩ የዋስትና ጥያቄዎች እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ ሲያከራክሩ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡በፖሊስ በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች በማታለልና ደረቅ ቼክ በመጻፍ ወንጀሎች የተከሰሱት ኤርሚያስ በአጠቃላይ 1.1 ቢልዩን ብር ዋስትና ተጠይቀው ቤተሰቦቻቸው ክፍያውን ቢፈጽሙም ሳይለቀቁ ቆይተዋል፡፡

ዋስትናው ተፈቅዶላቸው መያዣው ለፍርድ ቤቶቹ ገቢ ከተደረገ በኋላ ባለመለቀቃቸው የኤርሚያስ ጠበቃ ፖሊስን በመክሰስ ፍርድ ቤት ባቆሙበት ዕለት ፖሊስ የመኪናውን ጉዳይ ይዞ በመቅረብ ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡

ምንጭ ፎርቹን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.