የበቀለ ገርባ የፍትህ ሂደት በዘ-ህወሀት የዝንጀሮ (የይስሙላው) ፍርድ ቤት (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

unnamed
በአሜሪካ የሕግ አፈ ታሪክ የስኮፐስ የዝንጀሮ (የይስሙላ) ፍርድ ቤት ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ በ1925 ጆን ስኮፐስ ተብሎ የሚጠራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በቴኔሲ ግዛት ድንጋጌን በመጣስ በአንድ የሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሰው ልጆች ዘገምተኛ ለውጥ/human evolution ሲያስተምር ተገኝቶ እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ የስኮፐስ የፍርድ ሂደት ጉዳይ ልጆቻቸው በዘመናዊ ትምህርት እንዲታነጹ በማይፈልጉ ምንም በማያውቁ ደንቆሮዎች እና ሌሎች ደግሞ ዘመናዊውን የአሜሪካ የሳይንስ ትምህርት እንዲገበዩላቸው በሚፈልጉ ሰዎች መካከል የሚደረግ ትግል ስለነበር የፍርድ ሂደቱ በመላው ዩኤስ አሜሪካ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲታይ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2016 የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) በበቀለ ገርባ እና በሌሎች በ21 ሰዎች ላይ የእራሱን የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 በመጠቀም የሸፍጥ ክስ መስርቶባቸው የዉሸት ፍርድ ሂደቱ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

በቀለ ገርባም እንደዚሁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ/እንግሊዝኛ የሚያስተምር ፕሮፌሰር መምህር ነው፡፡ ሆኖም ግን ያልተማሩትን ልጆች በማስተማሩ አይደለም ክስ የተመሰረተበት፡፡ የእርሱ ወንጀሎች የሚከተሉት ናቸው፡

1ኛ) ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ እያደረሰ ያለውን አስደንጋጭ ሰይጣናዊ ወንጀሎች ለኢትዮጵያ ሕዝቦች በማስተማሩ እና በማሳወቁ፣

2ኛ) ዘ-ህወሀት በኦሮሚያ ክልል ሲፈጽም የነበረውን ገደብ የሌለው  የሰው ልጆች እልቂት በማጋለጡ፣ እና

3ኛ) በዘ-ህወሀት እየተደረገ ያለውን አይን ያወጣ የመሬት ቅርምት ሙስና፣ በሰው ልጆች ላይ ጭካኔ የተመላበት ግድያ እየፈጸመ መሆኑን እና ዘ-ህወሀት መቋጫ የሌለው ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ የመጠቀም አባዜውን በማጋጡ ምክንያት ነው፡፡

በዚህ ሸፍጥ በተመላበት የዘ-ህወሀት የአሸባሪነት ክስ ከበቀለ ጋር አብረው እንዲከላከሉ የሸፍጥ ክስ የተመሰረተባቸው የሚከተሉትን ወገኖቻችንን ያካትታል፡

1ኛ) ጉርሜሳ አያኖ ወይሳ፣

2ኛ) ደጀኔ ጣፋ ገለታ፣

3ኛ) አዲሱ ቡላላ አባዋልታ፣

4ኛ) አብደታ ነጋሳ ፈዬ፣

5ኛ) ገላና ነገራ ጅማ፣

6ኛ) ጭምሳ አብዲሳ ጃፋሮ፣

7ኛ) ጌቱ ግርማ ቶሎሳ፣

8ኛ) ፍራኦል ቶላ ዳዲ፣

9ኛ) ጌታቸው ደረጀ ቱጁባ፣

10ኛ) በየነ ሩዳ ደጁ፣

11ኛ) ተስፋዬ ሊበን ቶሎሳ፣

12ኛ) አሸብር ደሳለኝ በሪ፣

13ኛ) ደረጀ ነርጋ ደበሎ፣

14ኛ) ዩሰፍ አለማየሁ ሄረጋ፣

15ኛ) ሂካ ተክሉ ቁጡ፣

16ኛ) ገመቹ ሻንቆ ገዲ፣

17ኛ) መገርሳ አስፋው ፈይሳ፣

18ኛ) ለሚ ኢዴቶ ገረመው፣

19ኛ) አብዲ ታምራት ደሲሳ፣

20ኛ) አብዲሳ ኩምሳ ሂሳ፣ እና

21ኛ) ሀልኬኖ ቆንጨራ ጎሮ

ናቸው፡፡

ባለፈው ሳምንት በበቀለ እና በሌሎች ተከላካይ ጓደኞቹ ላይ የሸፍጥ ክስ በቀረበባቸው ጊዜ የዘ-ህወሀት የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል የኗሪው ሕዝብ መሬት መብት ማስጠበቅ መሪ በነበሩት በኦኬሎ አክዋይ ኦቻላ ላይ ተመስርቶ በነበረው የአሸባሪነት የሸፍጥ ክስ የ9 ዓመታት እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡ ኦኬሎ በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የቀድሞ የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ የነበሩ እና ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ ሲፈጽማቸው በነበሩት ኢሰብአዊ ወንጆሎች ተማርረው እ.ኤ.አ በ2004 ወደ ኖርዌ ሀገር ተሰድደው ሲኖሩ የቆዩ ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ መጋቢት 2014 ዘ-ህወሀት ከደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ቡድኖች ጋር በመመሳጠር ኦኬሎ ደቡብ ሱዳንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ታፍነው ወደ ኢትዮጵያ እንዲወሰዱ አድርጓል፡፡ (በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ የቀረበውን የኦኬሎን የክስ መከላከያ ለማንበብእዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2014 የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነጻነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እየተባለ የሚጠራው የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ቡድን ዋና ጸሐፊ የነበሩትን አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን መንግስት አባላት ጋር በመመሳጠር ሕገወጥ በሆነ መልኩ ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ ወስዷቸዋል፡፡

ህወሀት በበቀለ ገርባ እና በሌሎች 21 ሰዎች ላይ የመሰረተው የአሸባሪነት የሸፍጥ ክስ፣
Bekele Gerbaበበቀለ እና በሌሎች 21 ሰዎች ላይ የተመሰረተው የሸፍጥ የውንጀላ ክስ የካፍካ የፍርድ ሂደት ቀጥታ ግልባጭ ነው፡፡ ያ ረዥም ታሪክ እንዲህ በሚለው ዓረፍተ ነገር ይጀምራል፡ “አንድ ሰው በጆሴፍ ኬ. ላይ ውሸት መናገር አለበት፣ እርሱ ምንም ዓይነት ስህተት እንዳልሰራ ያውቃል፣ ሆኖም ግን ከዕለታት አንድ ቀን ጠዋት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡“

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በቀለ እና ሌሎች 21 ተከላካይ ሰዎች ምንም ዓይነት ስህተት እንዳልሰሩ እያወቁ በዘ-ህወሀት በቁጥጥር ስር ሲውሉ አንድ ሰው ውሸት መናገር አለበት፡፡

የዘ-ህወሀት “የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001“ እየተባለ የሚጠራው ግራ የሚያጋባ እና የዘፈቀደ የአሸባሪነት የክስ ውንጀላ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፡ “በቀለ ከማጎሪያው እስር ቤት መፈታቱን ተከትሎ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)/Oromo Federalist Congress ባለስልጣን በመሆን ወደ ዩኤስ አሜሪካ በመሄድ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)/Oromo Liberation Front መሪዎች ጋር ይገናኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ እና የኦነግን አሸባሪ መልዕክት በማሰራጨት አመጽ እና ነውጥ ሊያስፋፋ ነው ተብሎ ተወነጀለ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከሌሎች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ወደተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የአሸባሪነት ድርጊት ለመፈጸም የሚያስችሉ ትዕዛዞችን ሰጥተዋል ተብለው ተወነጀሉ፡፡ በቀለ በኦነግ ስም የኦፌኮ አባላት የሽብር ድርጊት እንዲፈጽሙ እና የመንግስት ተቋማትን፣ መንገዶችን የማውደም እና በጸጥታ ኃይሎች ላይ የጥቃት እርምጃ እንዲወስዱ አስተባብሯል ተብሎ ተወነጀለ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቀለ ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ እና የአመጽ ቅስቀሳ በማድረግ የበርካታ ሰው ህይወት እንዲጠፋ እና ንብረት እንዲወድም አድርጓል በማለት ተወንጅሏል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በሌሎች ተከላካዮች ላይ የቀረበው የውንጀላ መክተፊያ ቢላዋ በኦነግ ስም ሆነው የአሸባሪነት ድርጊት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል የሚል አንድ ዓይነት መልዕክትን የሚደግም ነው፡፡“

የሽብርተኝነት የፍርድ ሂደት በዘህወሀት የዝንጀ/የጦጣ ፍርድ ቤት፣

የዘ-ህወሀት የፍትህ ዘርፍ እንደ ፍትህ ስርዓት ቅንነት በሌለው፣ በሙስና እና  በምዕናባዊ ስሜታዊነት ተግባራት ላይ የተመሰረተ የሸፍጥ የፍትህ ሂደት እንደሆነ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ስናገር ቆይቻለሁ፡፡

“የጦጣ የፍርድ ቤት ሂደት በዝንጀሮው ፍርድ ቤት”  በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ታህሳስ 2007 አቅርቤው በነበረው ትችቴ የዘ-ህወሀት የፍትህ ስርዓት ነጻ የሆኑ ሰዎችን የጥቃት ሰለባ ለማድረግ የተዘጋጀ ኢፍትሀዊ ስርዓት እንደሆነ ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት ሞክሪያለሁ፡፡ የዘ-ህወሀትን የፍትህ ስርዓት የካንጋሩ/ጦጣ ፍርድ ቤት በማለት እየገለጽኩበት ያለው ሁኔታ ለጥቂት አንባቢዎቼ ግልጽ ላይሆንላቸው ይችላል፡፡

የካንጋሩ ፍርድ ቤቶች የሚለው ቃል በአውስትራሊያ ከሚገኙ ካንጋሮዎች ወይም ደግሞ የልጆቻቸው መሸከሚያ ከረጢት ካላቸው ማናቸውም አጥቢ እንስሳዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡ ሀረጉ የሕግን ወይም የፍትህን ፍትሀዊ መለኪያ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል ዝም ብሎ በጭፍንነት የሚደረገውን የፍትህ ሂደት ለማመላከት ሲባል ከጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ የካንጋሩ ፍርድ ቤቶች፣

1ኛ)  የሕግ እና የስነ ምግባር ግዴታዎችን አሽቀንጥረው በመጣል ሆኖም ሕጋዊ በማስመሰል ሆን ብለው እውነታውን የሚዘሉ ወይም አላግባብ የሚተገብሩ እና የሕግ እና የስነምግባር ግዴታዎችን የሚያዛቡ ለታዕይታ ሲባል ብቻ የተቋቋሙ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ናቸው፡፡

2ኛ) በሕጋዊ መንገድ ሳይሆን ከሕግ አግባብ ውጭ ዜጎችን የፍትህ እጦት ሰለባ ለማድረግ ለማስመሰያነት የተቋቋሙ የውሸት ፍርድ ቤቶች ናቸው፡፡

በአፍሪካ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ለፖለቲካ ሸፍጠኝነት ጉዳዮች መጠቀሚያነት የሚውሉትን የተመሰረቱ የፍትህ ተቋማት “የዝንጀሮ /ጦጣ ፍርድ ቤት” የሚለውን ሀረግ ለመግለጽ እነዚህን ቃላት አጣምሪያለሁ፡፡ በጫካ በነበሩበት ጊዜ የዘ-ህወሀት መሪዎች በጫካው ፍርድ ቤታቸው የጫካ የፍትህ ስርዓትን ያራምዱ ነበር፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ እውቀት ወይም ማስረጃ ካላቸው ሰዎች እንደተገነዘብኩት በጫካ ህይወታቸው ጊዜ የዘ-ህወሀት ቁልፍ መሪዎች ስልታዊ በሆነ መንገድ ለወደፊት ተቀናቃኝ ጠላት ሊሆኑ የሚችሉትን፣ ሰላማዊ አመጸኞችን፣ ለምን የሚል ጥያቄ የሚያቀርቡትን ሞጋቾች፣ የወደፊት ጠላቶችን፣ ተቀናቃኞችን፣ ታማኝነት የላቸውም ተብለው በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩትን ወይም ጠላት ናቸው ተብለው የተፈረጁትን ሚስጥራዊ እና ድብቅ በሆነ መልኩ ማጥፋት፣ ማግለል ወይም ደግሞ ሌሎች እቀባዎች እንዲደረጉባው ያደርጉ ነበር፡፡ (እ.ኤ.አ በ2009 “የህወሀት የፖለቲካ ታሪክ/A Political History of TPLF” በሚል ርዕስ የቀድሞው የህወሀት መስራች የነበሩት አረጋዊ በርሄ ባዘጋጁት መጽሐፍ ውስጥ ከገጽ 182-3 የቀረበውን የዘ-ህወሀትን የጫካ ፍርድ ቤት ሂደትን የሚገልጸውን ክፍል ይመልከቱ፡፡)

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ1991 በኢትዮጵያ ስልጣንን ከተቆጣጠረ በኋላ ያደረገው ነገር ቢኖር በጫካ ውስጥ ሲተገብረው የቆየውን የጫካ የፍርድ ቤት ሂደት መጠኑን ከፍ የማድረግ እና አገር አቀፍ መልክ እንዲኖረው የማድረግ ስራ ነው፡፡ የዘ-ህወሀትን የጫካ ፍትህ ውርስ ነው አሁን የዝንጀሮ/ጦጣ ፍርድ ቤት ስርዓት እያልኩ የምጠራው፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ዘገባ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ በማለት ደምድሟል፡ “ሕጉ ነጻ የዳኝነት ስርዓትን ይፈቅዳል፡፡ የሲቪል/የፍትሐብሄር ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ የሆነ ነጻነትን ባካተተ መልኩ የሚሰሩ ቢሆንም ቅሉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤቶቸ ግን ደካማ፣ ከፍተኛ ሸክም የተጫነባቸው እና ለፖለቲካዊ ተጽዕኖ የተጋለጡ ናቸው“ ብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ደግሞ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቷል፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ የዳኝነት ነጻነት የለም እናም አሁን በቅርቡ እንደታዩት አንዳንድ በርካታ አጋጣሚዎች በሰላማዊአመጸኞች ላይ ሸፍጥን የያዘ ኢፍትሀዊነት ድርጊት ለመፈጸም እና የኃይል እርምጃ ለመውሰድ በስራ ላይ እየዋሉ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሲቪል ማህበረሰብ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የጸረ ሽብር አዋጁ የይስሙላ እና የዘፈቀደ አፈጻጸም እንዲኖራቸው የሚያጠናክር ህጎችን አውጥቷል“ ብሏል፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ዘ-ህወሀት እየተገበረው ያለው የፍትህ ስርዓት የሕግ የበላይነትን ያሰፈነ ቅርጽ ያለው፣ ፍትሀዊ እና ትክክለኛ በማስመሰል ምናባዊነትን በመፍጠር በዘ-ህወሀት ጠላት ላይ የሚመሰረት ማንኛውም ክስ የተበላ እቁብ የመሆኑ እውነታ የታወቀ ቢሆንም ቅሉ የፍርድ ቤት ሂደቱን ለእራሱ ኢፍትሀዊነት ድርጊቱ መጠቀሚያ ለማስመሰያነት ይጠቀምበታል፡፡ የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ጀግኒት የሆነችው እና የዘ-ህወሀት የሸፍጥ የአሸባሪነት ውንጀላ ክስ ሰለባ የነበረችው ርዕዮት ዓለሙ ውሸት ካልዋሸች እና በሀሰት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስም የማጠልሸት ድርጊት ካልፈጸመች የሞት ቅጣት እንደሚበየንባት ከዚህም አነሰ ቢባል የእድሜ ልክ እስራት እንደሚበየንባት የዘ-ህወሀት አለቆች ሀሰን ሽፋ እና ለይኩ ገብረእግዚአብሄር ሲያስፈራሯት እንደነበር በግልጽ ዘግባዋለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንደ ሸቀጥ በገበያ በዘ-ህወሀት መሪዎች እና ግብር አበሮች እንዲሁም ደጋፊ በሆኑት ስምየለሾች፣ የማይታወቁ እና አቅም የለሽ ድሁሮች በስልጣን ማማ ላይ ተቀምጠው ከሕግ አግባብ ውጭ በስውር በሚሰሩ ሰዎች ጠቅላይነት የሚሸጥበት እና የሚገዛበት የውሸት የፍትህ ስርዓት ሆኗል፡፡ በዘ-ህወሀት የፍትህ ስርዓት ውስጥ ዓለም አቀፋዊ የሕግ መርሆዎች፣ ፍትህ እና የሕግ የበላይነት ወደ ጎን የተጣሉ፣ የተናቁ እና በሸፍጥ የተሞሉ ናቸው፡፡ ድሆች፣ የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በተስፋ የተሞሉት ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ አማጺዎች፣ ተቃዋሚዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች መሪዎች በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የድንጋይ ዓይነት ጸጥታዊ ዝምተኝነት ምክንያት በሕጋዊነት ስም ተገድለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀት አገዛዝ መሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ እና ግብረ አበሮቻቸው ከሕግ በላይ የሆኑበት እና “ሕግ ማለት እኛ ነን” የሚሉበት ስርዓት ነው ያለው፡፡

ዩኤስ አሜሪካ የሚያሳስባትን ነገር ገለጸች፣

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 29/2016 የዩኡስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ ማድረግ ያለበትን እንዲህ የሚል የተሻለ ነገር አደረገ፣ “እ.ኤ.አ በ2015 መጨረሻ አካባቢ የኢትዮጵያ መንግስት በቁጥጥር ስር ባዋላቸው በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር በሆኑት በበቀለ ገርባ እና በሌሎች በአሮሚያ ክልል ውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ ለመመስረት ያሳለፈው ውሳኔ በጥልቅ አሳስቦኛል“ ይላል፡፡

ወይ ጉድ ምን አይነት አነጋገር ነው ?   አሳስቦኛል! ድንቄ ም!

የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ሁኔታ “አሳስቦኛል“ እያለ ሲያወጣው የቆየውን መግለጫ የምቆጥረው ቢሆን ኖሮ “በኢትዮጵያ የሚከሰተው የጸደይ አብዮት ቅሬታ ዩኤስ አሜሪካን ያሳስባታል“ በሚል ርዕስ መጽሐፍ ማሳተም እችል ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በማስመልከት ዘ-ህወሀት ምርጫውን መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ በማለት እምቧከረዩ ካለ በኋላ ኋይት ሀውስ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፣ ዓለም አቀፍ የምርጫታዛዚዎች ምርጫው ለም አቀፍ መስፈርትን የማያሟላ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፣ እናም ይኸ ጉዳይ ያሳስበናል“ ነበር ያለችው፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 እና በ2015 ተደረጉ በተባሉት የይስሙላ የቅርጫ ምርጫዎች ዩኤስ አሜሪካ ያው እንደተለመደው አንድ ዓይነት በሆነ መልኩ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛዚዎች ምርጫው ለም አቀፍ መስፈርትን የማያሟላ መሆኑን ይፋ፣አድርገዋል፡፡ እናም ይኸ ጉዳይ ያሳስበናል“ ነበር ያሉት፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2014 የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከዘ-ህወሀት ባለስልጣኖች ጋር በመገናኘት የኢትዮጵያ የዞን 9 ወጣት ጦማሪዎች በቁጥጥር ስር የመዋላቸው ጉዳይ ያሳሰበው መሆኑን ነበር የገለጸው፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ባራክ ኦባማ የዘ-ህወሀት አገዛዝ ዴሞክራሲያዊ ነው ከማለቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሱሳን ራይስ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አያያዝ ሁኔታ ዩኤስ አሜሪካን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ያሳስባታል ነበር ያለችው፡፡

ዘ-ህወሀት ሁልጊዜ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣውን ወንጀል፣ የምርጫ ስርቆትን እና ዓለም አቀፍ ሕጎችን ሁሉ በጣሰ ቁጥር ዩኤስ አሜሪካ “አሳስቦኛል” የሚለውን አሰልቺ ቃል እንደ በቀቀን ትደጋግመዋለች፡፡

በየጊዜው ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ ኢሰብአዊ ወንጀሎችን፣ በፈጸመ፣ ምርጫዎችን በሰረቀ እና ዓለም አቀፍ ሕጎችን በጣሰ ቁጥር ዩኤስ አሜሪካ “አስስቦኛል” በማለት መግለጫ ታወታለች፡፡

ድምጽን ከፍ አድርጎ በመጮህ “አሳስቦኛል” ማለት ምን ማለት ነው?

“አሳስቦኛል” ማለት “ከገዳይ ወሮበላ ዘራፊዎች ጋር አንድ አልጋ በመጋራታችን ሀፍረት ተሰምቶናል፣ ስለሆነም የዓለምን ማህበረሰብ ለማታለል እና ከገዳይ ወሮበላ ዘራፊዎች ጋር አንድ አልጋ ላለመጋራታችን የዓለም ሕዝብ እንዲያምነን እንፈልጋለን“ ለማለት የቀረበ የዴፕሎማሲ ቋንቋ ቃል ነውን?

ለእኔ ስለአንድ ነገር ያሳሰበው/ባት ሰው ስለዚያ ነገር ተገቢ የሆነ እርምጃ ይወስዳል/ትወስዳለች፡፡

ሰዎች የሌሎች ሰዎች ጤንነት እና ደህንነት ሲያሳስባቸው ዝም ብለው በቂጣቸው ተንዘርጥጠው አይቀመጡም ወይም ደግሞ “አሳስቦኛል” እያሉ ከንቱ የሆነ ዙረት አይዞሩም፡፡ ይልቁንም አንድ ነገር ያደርጋሉ፡፡

ዩኤስ አሜሪካ “አሳስቦኛል” ብትል ማን ጉዳዩ ነው? ዩኤስ አሜሪካ “አሳስቦኛል” ስትል ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ እልቂት መፈጸምህን እና የሰብአዊ መብቶችን መደፍጠጥህን አቁም ማለቷ ነውን?

ዩኤስ አሜሪካ “አሳስቦኛል” የሚለውን ቃል ስትጠቀም  ቢያንስ ይህንን ቃል በመናገሯ አንድ ነገር እንዳደረገች እራሷን ለማሳመን ነውን?

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን “አሳስቦኛል” ማለት ሌላ ምንም ዓይነት ነገር ሳይሆን አንድም ነገር አለማድረግ ማለት ነው፡፡

ዩኤስ አሜሪካ ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጽመው ኢሰብአዊ ወንጀል ከልቧ በእርግጠኝነት “አሳስቦኛል” የምትል ከሆነ ስለሚያሳስባት ጉዳይ ተጨባጭ የሆነ አንድ ነገር ማድረግ ይኖርባታል፣ ለምሳሌ ያህልም የምትለግሰውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እርዳታ እና ዓመታዊ የእርዳታ ፕሮግራም ማቋረጥ ይኖርባታል፡፡

“አሳስቦኛል” የሚለው በሌላ በየትም ሳይሆን በአሜሪካ የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ አስመሳይነት የዴፕሎማሲ መዝገበ ቃላት (ዲክሽነሪ) ውስጥ ብቻ የሚገኝ ቃል ነው፡፡

ለመሆኑ በቀለ ገርባ ማን ነው?

በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ መሪ ነው፡፡

በቀለ ሰላማዊ በሆነ ነገር ላይ የሚያምን እና ኃይል መጠቀምን የማይፈልግ፣ እራሱን ክርሲቲያን አድርጎ የሚቆጥር ለአራት ዓመታት በእስር ቤት ሲያሳልፍም የማርቲን ሉተርን ኃይማኖታዊ ንግግሮች ሲናገር የቆየ እና እነዚህንም ኃይማኖታዊ ቃሎች ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ በመተርጎም በቅርቡ በመጽሀፍ መልክ እንደሚወጣ ተስፋ አድርጎ ሲጠባበቅ የነበረ ሰላማዊ ሰው ነው፡፡

የመጽሐፉ ርዕሱም “ህልም ነበረኝ ” የሚል ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በቀለ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት መርማሪዎች ጋር ከተገናኘ በኋላ ዘ-ህወሀት በአሸባሪነት ክስ መሰረተበት፡፡

በቀለ እ.ኤ.አ ታህሳስ 2012 ብይን በተላለፈበት ጊዜ ለዘ-ህወሀት የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“በህይወቴ ዘመን ሁሉ ኢፍትሀዊነትን፣ አድልኦን፣ የዘር ልዩነትን እና ጭቆናን ስዋጋ ቆይቻለሁ፡፡  እኔው እራሴ ፈልጌው ሳይሆን በአምላክ ፈቃድ ለተፈጠርኩበት ለኦሮሞ ሕዝብ የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሳካሂድ የቆየሁት ሰላማዊ ትግል እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ያለአግባብ ክስ ቢመሰረትብኝም በሰላማዊ ትግሌ እኮራበታሁ፡፡ ይቅርታ እንድጠይቅ የሚፈቀድልኝ ቢሆን ኖሮ ይቅርታውን የምጠይቀው ባልሰራሁት ጥፋት ወንጀለኛ ካለኝ ከዚህ ፍርድ ቤት ሳይሆን አብረው በመኖራቸው ብቻ በከፍተኛ ደረጃ በመሰቃየት ላይ ላሉት ወገኖቼ ድምጼን ከፍ አድርጌ ባለመጮሄ ነበር…“

በቀለ ገርባ ማን እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለአንባቢዎቼ መናገር አልፈልግም፡፡

ለመናገር ብፈልግም እንኳ አልችልም፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ እርሱን ለመግለጽ የሚያስችል አንደበት ወይም ደግሞ ምዕናባዊ የስነጽሁፍ ችሎታ የሌለኝ እና አንድ ልዩ የሆነ ድፍረት፣ ታማኝነት እና ስብዕናን የተላበሰ እንዲሁም ለእናንተ መናገር የሚያስችል የልህቅና ተመሳስሎ የማይገኝለት ሰው ማለት ነው በቀለ ገርባ፡፡

በቀለም ከ”ጽንፈኛ” ወይም ደግሞ ከ”አሸባሪነት” ውጭ ሁሉን ነገር ማለት ነው፡፡

በቀለ ገርባን አሸባሪ ማለት ዘ-ህወሀትን ዴሞክራሲያዊ ቡድን ነው ብሎ እንደመጥራት ያህል ነው፡፡ (ባራክ ኦባማ ምንድን ነበር ያለው?!)

ዘ-ህወሀት “ዴሞክራት” ከሆነ በእርግጠኝነት በቀለ “አሸባሪ” ነው፡፡ አራት ነጥብ!

ይልቁንም ስለበቀለ ልዩ  የሆነው እውነታ ነገር ሌሎች በርካቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ በቀለ በዘ-ህወሀት ላይ ጠንካራ የሆነ ትችት የሚያቀርብ ሰው አይደለም፡፡

የበቀለ ሀሳቦች ሚዛናዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ በውል የታሰቡ እና በእውነታ ላይ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ተዘጋጅተው የሚገለጹ ናቸው፡፡ በቀለ በዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ ማሽን የማይበሳጭ እና ስሜታዊ በሆነ መልኩ እና ያለማቋረጥ ጽሑፎችን በዘፈቀደ እያወጣ የሚያሰራጭ ሰው አይደለም፡፡

በቀለ መቁረጥ የሚያስችል መጥረቢያ የለውም፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ያልተቀባባውን እና እንደወረደ ያለውን ጥሬ ሐቅ እንዳለ ይናገራል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ በነበረው የመሬት ቅርምት በቀለ ገርባ በእራሱ አንደበት የተናገረው ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡

ቪዲዮ እየተናገረ ያለው (ከታች ተተርጉሞ የቀረበው) በእውነት ስለእውነት በሚገባ ታስቦበት በውል ተጢኖ የተደረገ፣ ብሩህ፣ ዘርፈ ብዙ እውቀት ያለው፣ የሚያስብ፣ ነገሮችን በፍጥነት የሚገነዘብ እና ለሰው ልጆች ጥልቅ የሆነ ፍቅር ያለው ሰው ከመሆን ውጭ ሌላ የሚታይበት ነገር ስለመኖሩ  አንባቢዎቼ ፍርዳቸውን እንዲሰጡ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ (የቪዲዮ ምስሉን ለማየት እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡ ትርጉሙንም ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡)

እ.ኤ.አ በ2010 በቀለ ምን ዓይነት ስብዕና ያለው ሰው መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለዘ-ህወሀት እንዲህ በማለት አሳዬ፡

“…ኢህአዴግ [የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እና በዘህወሀት የሚመራው የፖለቲካ ሸል ኮርፖሬሽንየብዙሀን የፖለቲካ ፓርቲ ህብረትምዕናብን በመመስረቱ ረገድ ምንም ያደረገው ነገር የለም አንልም፡፡ ያደረገው ነገር እንዳለእምነታችን ነው ምክንያቱም ሀገሪቱ የመረጠችውን ነገር አድርጓል፡፡ ሀገርን መምራት እንዲህ ቀላል ነገር እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ሆኖም ግን ከዓመት ዓመት ኢህአዴግ የሕዝቡን ጥያቄ አይሰማም፣ ከእራሱ ተሞክሮ ለመሻሻል ወይም ደግሞ ለመማርአልሞከረም፣ እናም ህዝቡን እና ሀገሪቱን እንደሚጠበቀው ወደፊት ማስኬድ አልቻለም፡፡ ቀን በቀን ኢህአዴግ ወደኋላ እየሄደነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ መምራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ኖም ግን ኢህአዴግ ለዚህች ሀገር ምንም ነገርአላደረገም ወይም ደግሞ አላበረከተም ለማለት በፍጹም አንችልም 

እያቀረብኩት ባለሁት በዚህ ጽሑፍ ላይ ስለመሬት ባለቤትነት፣ ስለትክክለኛ የመሬት አጠቃቀም እና ስለልማት ውጤቶች ትኩረትለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እና ገየዥው ፓርቲ [ኢህአዴግሰነዶች