ደቡብ ሱዳን ‹‹የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው ገብተዋል›› መባሉን ‹‹ውሸት›› አለች

lul_ruai_koang_l_the_military_spokesperson_for_the_spla-io_and_james_gatdet_dak_spokesperson_for_riek_machar_r_speak_to_the_press_in_addis_abab_on_09052014_afp-af1f8

(ሳተናው) የደቡብ ሱዳን መከላከያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን ዘልቀው በመግባት የሙርሌ ጎሳ አባላት ከኢትዮጵያ ጠልፈው የወሰዷቸውን ልጆች ለማስለቀቅ እየተንቀሳቀሱ ነው በማለት የተሰራጩ ዘገባዎችን ውሸት በማለት አጣጥሏል፡፡

‹‹የደቡብ ሱዳን መከላከያ ኃይል የተሰራጨውን እውነተኛ ያልሆነ ፕሮፓጋንዳ ለማስተካከልና እውነቱን ለመግለጥ ይፈልጋል፡፡በማህበራዊ ድረ ገጾች የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ስለመግባታቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡ይህ ሙሉ ለሙሉ ትክክል ያልሆነ መረጃ ነው፡፡እውነተኛውና ትክክለኛው መረጃም የኢትዮጵያ ወታደሮች በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ ቲርጉልና ፖቻላ በሚባሉ ቦታዎች መስፈራቸው ነው›› ያሉት የደቡብ ሱዳን መከላከያ ኃይል ብርጋዲየር ሉቲናንት ሩዊ ኮአንግ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች እጋራቸውን በደቡብ ሱዳን ክልል ሳያስገቡ ድንበር ላይ የሰፈሩት በሙርሌ ታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ 100 ልጆችን ለማስለቀቅ መሆኑን ባለስልጣኑ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ወታደሮች በሁለቱ አገራት የጋራ ድንበር ዙሪያ መስፈር መጀመራቸውን በይፋ የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ምክንያቱም በከፍተኛ ደረጃ የጣጠቁ የሙርሌ ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ ክልል ዘልቀው በመግባት 200 ሰዎችን በመግደል 100 ልጆችን ጠልፈው በመውሰድ 2000 እንስሳትን ዘርፈዋል››ብለዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ መታጠቃቸው የተነገረላቸው ሙርሌዎች ወደ ጋምቤላ ክልል በመዝለቅ 13 የኑዌር ጎሳ አባላት መኖሪያ መንደሮችን በማጥቃት ግድያና አፈና መፈጸማቸው አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከጥቃቱ በኋላ ወታደሮቻቸው ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው በመግባት ታፍነው የተወሰዱትን ልጆች እንደሚያስመልሱ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ኮአንግ ‹‹የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ባልስልጣን ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ አምርተዋል››ብለዋል፡፡የሁለቱ አገራት መከላከያ ሚንስትሮች ታፍነው የተወሰዱትን ልጆች ለማስለቀቅ በጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ኮአንግ አስታውቀዋል፡፡

በዘመቻው ስኬታማ ለመሆንም የደቡብ ሱዳን መከላከያ ኃይል አምስት አባላት ያሉበትን ኮሚቴ በማዋቀር ከኢትዮጵያ ሰዎች ጋር ለመስራት ተዘጋጅተዋል፡፡በኮሚቴው ውስጥም የደቡብ ሱዳን መከላከያ ምክትል ሚንስትርና የቦማ ክልል ገዢ እንደሚሳተፉ  ቦአንግ ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች መቼም ቢሆን ክልላቸውን ጥሰው እንዲገቡ እንደማያደርጉ ቦአንግ በማስታወቅም ‹‹ለህዝቡ አንድ ነገር ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ የአገራችን ድንበር በኢትዮጵያ ወታደሮች ስለመደፈሩ በማህበራዊ ድረ ገጾች የተሰራጨው ዘገባ ውሸት ነው፡፡ይህ የሚደረግበትም አግባብ አይኖርም››ብለዋል፡፡

ምንጭ ሱዳን ትሪቡን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.