ኬንያ ስደተኞችን ‹‹ወደመጣችሁበት ተመለሱ››እያለች ነው

An overview of the part of the eastern sector of the IFO-2 camp in the sprawling Dadaab refugee camp, north of the Kenyan capital Nairobi seen on April 28, 2015.  AFP PHOTO/Tony KARUMBA        (Photo credit should read TONY KARUMBA/AFP/Getty Images)
(ሳተናው) የአለማችን ትልቁ የስደተኞች ካምፕ ዘላለማዊ ይመስላል፡፡የመጀመሪያው የስደተኞች ድንኳን በበረሃማው ሜዳ የተደኮነው ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት ነበር፡፡በአሁኑ ወቅት የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚሸፍነው አካባቢ 50 ስኩዌር ኪሎ ሜትር(20 ስኩዌር ማይልሶችን)ነው፡፡

በኬንያና ሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ 344.000 ስደተኞች መራራውን የስደት ህይወት ይገፋሉ፡፡በካምፑ ከሚገኙት ስደተኞች የሚበዙት ሱማሊያዊያን ይሁኑ እንጂ ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት የተሰደዱም ይገኙበታል፡፡

ከዳዳብ በመቀጠልም ለ180.000 ስደተኞች መጠለያ የሆነውን ካኩማ የተባለውን ካምፕ በደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ ድንበር አቅራቢያ በኬንያ ግዛት ውስጥ ያገኛሉ፡፡የዚህ ካምፕ ዕድሜም እንደመጀመሪያው 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የመጀመሪያዋን ድንኳን የተከሉት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ስለመሆናቸው ይነገራል፡፡በኢትዮጵያ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ ብዛት ያላቸው የቀድሞው መንግስት ወታደሮችና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በካኩማ የስደት ህይወት ለመጀመር ካምፑን ቆርቁረዋል፡፡

የኬንያ የአገር ውስጥ ሚንስትር ባሳለፍነው ወር ባወጣው የመጨረሻ መግለጫ ሁለቱን የስደተኛ ካምፑች መዝጋት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ባለፈው ዓመት በኬንያ ጋሪሳ ዩኒቨርስቲ የአልሻባብ ታጣቂዎች 147 ተማሪዎችን መግደላቸውን ተከትሎ ኬንያ ሽብርተኞቹ በካምፑቹ የሚገኙ ስደተኞችን በመጠቀም እያጠቃኝ መሆኑን ደርሼበታለሁ በማለት እንደምትዘጋቸው ዝታ ነበር፡፡ሁኔታውን ለማብረድም የአሜሪካው ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ወደ ናይሮቢ በመምጣት ኬንያ ሐሳቧን እንድትቀይር አድርገው ነበር፡፡

አሁን ነገሮች የምር ተደርገው የተወሰዱ ይመስላሉ፡፡በናይሮቢ ስደተኞችን በመቀበል ምዝገባና ወደ ካምፑቹ ይወስዱ የነበሩ የጉዙ ሰነዶችን ይሰጡ የነበሩት ሁለት የስደተኞች መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡

በየዕለቱ ከ70 -100 የሚደርሱ ደቡብ ሱዳናዊያን በኬንያ የስደት ህይወት ለመጀመር ይመጣሉ፡፡እነዚህን ተቀብለው ይመዘግቡ የነበሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ በመደረጋቸውም ስደተኞቹ በአገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ እንደገቡ እንዲቆጠር ያደርጋቸዋል፡፡

በኬንያ የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች ለወቅታዊው የመንግስት ውሳኔ ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው መቸገራቸውን እየገለጹ ነው፡፡የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት መግለጫ በማውጣት መንግስትን ተማጽኗል፡፡ነገር ግን የአገር ውስጥ ሚንስትሩ ካራንጃ ኪቢቾ ‹‹በ2005 በዌስት ጌት የገበያ ማዕከል የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ በኬንያ የተደረጉ የሽብር ጥቃቶች የታቀዱትና የተፈጸሙት ከዳዳብ ነው፡፡እንዲህ አይነት ጥቃቶችን አሸባሪዎቹ በካምፑቹ የሚገኙትን ሰዎቻቸውን ባይጠቀሙ ኖሮ ሊፈጽሟቸው አይችሉም ነበር››ይላሉ፡፡

ምናልባት ኬንያ ካምፑቹን እዘጋለሁ በማለት የመናገሯ ዋነኛ መንስኤም ገንዘብ ፍለጋ ይሆናል፡፡ኪቢቾ በመግለጫቸው ስለዚሁ ጉዳይ ማንሳታቸው አልቀረም፡፡ አለም አቀፍ ለጋሾች ፊታቸውን ከኬንያ አውሮፓን እያጥለቀለቃት ወደሚገኘው የስደተኞች ጉዳይ በማዞር ለቱርክ የ6ቢልዩን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ብለዋል፡፡በሚንስትሩ እምነት ኬንያ ከምዕራባዊያኑ ከቱርክ የበለጠ ድጋፍና ትኩረት ሊደረግላት ሲገባ ይህንን አላገኘችም፡፡

በሶማሊያ የሚገኘውና ኬንያ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘችበት የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር በያዝነው ወር መጨረሻ ከተባበሩት መንግስታት አዲስ ውል እንደሚቀርብለት ይጠበቃል፡፡በዚህ ሁኔታ ውስጥም ግማሽ ሚልዩን የሚሆኑ ስደተኞችን ወደአገራቸው መመለስ የማይታሰብ ይሆናል፡፡ከዚህ አንጻርም የኬንያ ዛቻና ማስፈራሪያ ፈንድ ከማግኘት ጋር የተቆራኘ ሊሆንና ይህንኑ በማግኘትም ሊቋጭ ይችላል፡፡

በኬንያ በካኩማና ናይሮቢ ከ25.000የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደሚኖሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ ዴይሊ ኔሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.