ጎሰኝነት የሰው ልጅ ጠላት (ጌታቸው ኃይሌ)

በየጊዜው የሚታተሙት ዜናዎች፥ አሳቦችና አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት፥ የኢትዮጵያ በአንድ ሀገርነት መቀጠል ጎሰኝነት አደጋ ላይ እንደጣላት ብዙዎቻችን አምነናል። ጎሰኝነት እንደ ናዚዝም እና እንደ ፋሺዝም የሰው ልጅ ጠላት ነው።

ሕዝቡ ይጠየቅ፤

Getachew-Haile-አደጋው እንዳይደርስ የሚጥሩትም እንዲደርስ የሚገፋፉም ወገኖች ድምፃቸው እኩል ይሰማል። ሁለቱም ወገኖች “ሕዝቡ ይጠየቅ” እያሉ በሕዝብ ስም ይምላሉ። መሐላው ቢያንስ ሦስት ጕልሕ ችግሮች አሉት፤ አንደኛ፥ ሕዝብ የሚጠየቀው ብዙ ሀገሮችን አንድ ሀገር ለማድረግ እንጂ አንድን ሀገር ብዙ ሀገሮች ለማድረግ አይደለም። ይኸንን እክል ውድቅ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች የሶቪየት አንድነትንና የዩጎዝላቪያን መፈራረስ፥ የቸኮዝሎቫኪያን ሁለት አገሮች መሆን ለምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ሆኖም እነዚህ ሀገሮች የተከፋፈሉት የፈጠሩት የነፃ ሀገሮች አንድነት አልሠምር ስላለ ነው። አልሠምር ስላለ፡ ቀረ። ኢትዮጵያ ግን ቆዳዋ ሲጠብ ሲሰፋ የኖረች አንድ አገር እንጂ የነፃ ሀገሮች ስብስብ አይደለችም። የሀገር ገዳዮች ግፊት ወደቀድሞው እንመለስ ሳይሆን፥ አንድ ፍሬ ስትቀበር ብዙ ፍሬ እንደሚወለድባት ኢትዮጵያን እንቅበርና ብዙ አገሮች እናስወልዳት ነው። እነዚህ ሰዎች የረሱት አገሮቹ ሲወለዱ የተጠላውን የባህል ጭቆና ይዘው መሆኑን ነው፤ ማለትም፥ የአሁኒቱ ኢትዮጵያ እንድትከፋፈል የተፈለገው ከባህል ጭቆና ለመዳን ከሆነ፥ የባህል ጭቆና የሌለበት አገር አይወለድም። ልዩነቱ ለያንዳንዱ አዲስ አገር አዲስ ጨቋኝ ማንገሥ ነው።

ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.