ግንቦት 20: ኢትዮጵያውያን ወደ ቀድሞ ክብራቸው = ሕወሓታውያን ወደ ቀድሞ ጫካቸው

ምንሊክ ሳልሳዊ

1326የግንቦት ሃያን ሃያአምስተኛ አመት ‘የደርጎች መተካካት’ መሪ ቃላቸው ወደ ቀድሞው ክብራችን እንመለሳለን የሚል መሆኑ እጅግ አስገራሚና አስደማሚ ነው::ጥሩ መልእክት አለው::ኢትዮጵያ ሃገራችን በገዳይ ወታደሮች 17 አመታት በትግሪኛ ተናጋሪ ካንሰሮች ሃያ አምስት አመታት ክብሯን አጥታለች::ይህ ደግሞ ማንም የሚክደው አይደለም::ዘመናዊነትን ካላበሱን ሰው ካደረጉን በንጉሰ ነገስታችን ምንሊክ እንዲሁም በአድሃሪውና ጨቋኙ የሃይለስላሴ መንግስት ዘመን ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የነበራትን ዝና ስም ክብር አሁን የለም::ሕዝቡን የሚጨፈጭፍ እንጂ ሃገሩን የሚጠላ መሪ በታሪኳ ገጥሟት የማታውቀው ኢትዮጵያ በባንዳ ልጆች እጅ ገብታ ፍዳዋን እያየች ሕዝቧም ክብሩን አጥቶ ተዋርዶ አንገቱን ደፍቶ ይገኛል:: በሃገር ቤት ብቻ ሳይሆን በሰው አገር ኢትዮጵያዊነት ለብሄራዊ ውርደት ተዳርጓል::ኢትዮጵያውያን ተፈጅተዋል::ባለፉት 25 አመታት:: ስኳርና አፈር ደባልቆ መብላት ሲል መላስ የለመዱ ሕወሓቶች 10 የስኳር ፋብሪካ ውጠው ቁጭ ብለዋል::

አሁን ልብ ያለው የሚገባው ካለ ወደ ቀድሞ ክብራችን እንመለስ በማለት ወያኔ ራሱ እየነገረን ነው::ባለፉት 25 አመታት ክብራችንን አተናል::ባለፉት 25 አመታት ተሰደናል::ባለፉት 25 አመታት ተገድለናል::ባለፉት 25 አመታት ታስረናል:: ባለፉት 25 አመታት ተሳቀናል::ባለፉት 25 አመታት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀውሶችን አስተናግደናል::ባለፉት 25 አመታት ሃገራችን እና ሕዝባችን በአለም የዲፕሎማሲ መድረክ ውርደትን አስተናግደዋል::ባለፉት 25 አመታት ልጆቻችንን ለበረሃና ለባሕር ገብረናል::ባለፉት 25 አመታት በሃሰት ፕሮፓጋንዳ እና በሃሰት የኢኮኖሚ እድገት ሆዳችንን በባዶ ነፍተውንቃል::ባለፉት 25 አመታት የሃገሪቷ አንጡረ ሃብት በትግሪኛ ተናጋሪ ካንሰሮች እና ግብረአበሮቻቸው ተዘርፏል::ባለፉት ሃያ አምስት አመታት በሃገርና እና በሕዝብ ላይ የተሰራው ወንጀል ተዘርዝሮ አያልቅም::ይህን ደሞ ሃገር ወዳዶች ብቻ ሳይሆኑ የወያኔ ካድሬዎችን የሚስማሙበት ሳይፈሉ የሚውጡት ሃቅ ነው::ባለፉት 25 አመታት ያጣነውን ክብራችንን ወደ ቀድሞ ክብራችን ለመመለስ የዜግነት ግዴታችንን መወጫው ወሳኝ ወቅት ላይ ነን::

ግንቦት 20 የወታደራዊ ጁንታ ተወግዶ በእርስ በእርስ ጦርነት የጥቂት ዘረኛ ካንሰሮች ጁንታ የተተካበት የአምባገነን ጉልቻው የተለወጠበት ቀን እንጂ የድል ቀን አይደለም::ወንድም ወንድሙን ገሎ ወንድም ወንድሙን አፈናቅሎ ቤተሰብ በትኖ ወዘተ.. ጀግና ነኝ በሚልበት የሕወሓት ጉራ ውስጥ ምንም ድል የለም::ለነጻነት እና ለዲሞክራሲ በተሰዉ ወጣቶች በምእራባውያን እርዳታ በአማራው ገበሬ መንገድ ጠረጋ በገንዘብ በተደለሉ የደርግ መኮንኖች ሴራ ለስልጣን የበቃው ሕወሓት መራሹ ኢሕኣዴግ ዛሬ ጫካ ውስጥ የለመደውን የሕዝብ ደም መጠጣት ዘረፋ እና ውሸት በተደራጀ እና በዘመነ መልኩ አጠናክሮ ቀጥሎበታል::ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቡ መንግስታዊ ሌቦችን ፈጠረ እንጂ ምንም አልፈየደም::በየእስር ቤቱ የታጎሩ ንጹሃንን ፈጠረ እንጂ ምንም አልፈየደም:; ግንቦት 20 በአጠቃላይ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን ውርደት ያሰፋ ግድያ እና እስርን ያመጣ ፍትህን የቀበረ የመሳሰሉት ችግሮችን የፈጠረ ትኩይ ቀን ነው::ግንቦት 20 – ኢትዮጵያውያን ወደ ቀድሞ ክብራቸው = ሕወሓታውያን ወደ ቀድሞ ጫካቸው ….

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.