ኢሳት ሰበር ዜና – የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ተባረሩ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ተባረሩ። በምትካቸው ሌላው የአድዋ ተወላጅ አቶ ሀደራ አበራ ቦታውን ይዘዋል። የአቶ መለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ የነበሩት አቶ ኢሳያስ በዚያው መስሪያ ቤት ውስጥ አብራቸው ከምትሰራው ባለቤታቸው ጋር መባረራቸው በህወሀት ውስጥ ያለውን የስልጣን ፍጥጫና ቀጣዩን የሃይል ሚዛን የሚያመላክት ነው። በአቶ ኢሳያስ ላይ የተወሰደው እርምጃ ትልቅ ክስተት ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከልጃቸው ሰመሀል መለስ ጋር ቅዳሜ አሜሪካ ገብተዋል። ተያያዥነት ይኖረው ይሆን?