ዜና መረጃ — በረከት ስሞን አርበኞች ግንቦት 7 ያለዉ ዉስጣችን ነዉ ይላሉ!!

በልኡል አለም

Bereket 5- satenaw
ወሎን ሰፈር ተሻግሮ ሩዋንዳ ሙልሙል ዳቦ አካባቢ ወደ ቦሌ በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ይገኛል ከዩኒቨርሲቲዉ በተጓዳኙ በስተግራ ካለዉ ነጭ ህንጻ ላይ በደረጃ ቀስ እያልን ወደ 5ተኛ ፎቅ አመራን፣ ከቢሮዉ በተያያዘ ቱሪዝም ኤጀንሲ ባጎራባች ሲኖር ከስሩ ደግሞ ሱፐር ማርኬት አለ በዋናነት ወደዛ የሄድንበት ምክንያት የበረከት ስሟን ቢሮ እዚያ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ መሰረት ነዉ።

ቢሮዉ እነደደረስን ጸሐፊዉን ለማግኘት ትንሽ ብንጠብቅም አግኝተን አናገርናት የበረከት ስሞን ቢሮ መሆኑን ካረጋገጥን በኍላ ትንሽ ጠብቁ ተብለን ተቀመጥን ከጥቂት ቆይታ ወዲህ በረከት በሁለት ሰዎች መካከል ሆኖ ከተፍ ሲል ተመለከትነዉ የመሰብሰቢያ፣ ቢሮ በመሰለዉ ቢሮ ዉስጥ በአይኑ ሁላችንንም ገርበብ አድርጎን በአንገቱ ሰላምታ  ሰጥቶን  ወደ ዉስጥ ዘለቀ!

እኛም እዚያዉ መጠበቅ ጀመርን ከጥቂት ቆይታዎች በኍላ እቃ እንደረሳንና በሌላ ቀን እንደምንመለስ ለጸሐፊዋ ነግረን ተመልሰን ወጣን።

መኪናችን ዉስጥ ገብተን ወደተቀመጥንበት ሆቴል ገሰገስን ክፍላችን ዉስጥ እንደገባን መቀረጸ ድምጻችንን በቢሮዉ ዉስት እንደምን ጥለነዉ እንደወጣን እየተወያየን ተዝናናን ክትትላችንንም በመጠኑ በተለያዩ አካሎቻችን በማከናወን መግቢያ መዉጫቸዉን አጠናን ከ3 ቀናት በኍላ የተቀረጸዉን ድምጽ በጥቂቱ ይህን ይዟል።

— አቶ በረከት… አርበኞች ግንቦት 7 በየሐገሩ በየቦታዉ የተደራጀ ሐይል አለዉ ከእንግዲህ አ/ግንቦት 7 ልግባ መንገድ ልቀቁልኝ ወይም አሳልፉኝ አይልም ከእንግዲህ አ/ግንቦት 7 ገፍትሮንም አይገባም አ/ግንቦት 7 ያለዉ ዉስጣችን ነዉ!  ከባዱ ስራ የሚሆነዉም ይህዉ ነዉ! የሚጠረጠሩ ግለሰቦች በሙሉ የመኖሪያና የመስሪያ ቦታቸዉ ድረስ እየተዞረ የፎቶና የተለያዩ ተጨባጭ መረጃዎች ይያዝ!  ያለበለዚያ ምን እንደምንሰራ አይገባንም።

— አቶ ሳህረ የሚባል የብሄራዊ መረጃ ተወካይ…. በትክክል ብለዋል አቶ በረከት አባሎቻችን መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ነዉ የመጣነዉ እንዲሁም ከማህበራዊና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ የመጣነዉ እያሉ ቤት ለቤት ሁሉ እየዞሩ ነዉ። ግን መረጃዎችን ለማግነት ይህ ብቻ በቂ ነዉ ብለን አናስብም።

በሌላኛዉ እለት እዚያዉ ቢሮ ተገኘንና አቶ በረከትን አነጋግረን ድምጸ መቅረጻችንን ካስቀመጥንበት አንስተን ወጣን እንግዲህ በአሁኑ ወቅት ወያኔ ይህዉ ነዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!