ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በባለቤታቸው በወ/ሮ ሶፍያ አማካኝነት በገነቡት የአስመጪና ላኪ የንግድ ድርጅት በሜቴክና በመከላከያ ስም ያለ ቀረጥ ከውጭ ያስገባሉ

በሚያገኙትም ትርፍ በአዲስ አበባ እና በትግራይ በርካታ የሪል ስቴት ግንባታዎችን አካሂደዋል። ጄ/ል ሳሞራ በባለቤታቸው ስም ካስገነቡዋቸው ግዙፍ የንግድ ማእከሎች መካከል ቄራ አካባቢ ገብሬል ቤተክርስቲያንን አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶፊያ የንግድ ማእከል Sofina Mall የተባለው አንዱ ነው። ሶፊያ ሞል ለንግድ እንቅስቃሴ አመቺ በሆነ ሰፊ ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ባንኮች፣ የመድህን ድርጅቶች፣ ካፌዎች፣ የልብስና የጫመ መደብሮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የፎቶ ስቱዲዮዎች፣ የመኪና አከራይ ድርጅቶች ፣ ኢትዮ ቴልኮምና ሌሎችም በርካታ ደርጅቶች ተከራይተውታል። ሰፊ የመኪና ማቆሚያ ( ፓርኪንግ) ያለው ይህ የንግድ ማእከል በየወሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለጄ/ል ሳሞራና ባለቤታቸው ያስገባል። የህንጻውን የውስጥ ክፍል በተመለከተ የኢሳት ወኪል የቀረጸውን ቪዲዮ በዛሬው የኢሳት ቴሌቭዝን ይከታተሉ::

ምንጭ፦ኢሳት

Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.