ህወሃት ባለስልጣን ለትግራይ ነጻ አዉጭዉ ቡድን አጭር ማስጠንቀቀያ ሰጡ

በልኡል አለም
በስሞኑ ባደረግነዉ ስብሰባ ላይ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ወደ ህዝቡ እንድንመለስ ጥረት ለማድረግ ሞክሬያለዉ።

በዚያች ወሳኝ በሆነች ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የተካተቱት አጀንዳዎች ፈጽመዉ በትኩረት አለመታየታቸዉን እየገለጽኩ ነገር ግን ብዙዎች የምንመስል ጥቂቶች መሆናችንን ግምት የወሰድኩበት ትልቅ እለት መሆኑን ላስገነዝባችሁ እወዳለዉ!

በመሆኑም አሁን ማድረግ ያለብን አንድና አንድ ነገር ብቻ መሆኑን ስገልጽላችሁ በማስጠንቀቅ ጭምር ነዉ።

እናንተ እንደምትሉት ሲ.አይ.ኤ የአርበኞች ግንቦት 7ን ቀኝ እጅ ይዟል! እናንተ እንደምትሉት በራሳችን ሚዲያዎች ዉስጥ ተአማኒነታችንን ሊያሳጣ በሚችል መልኩ ሲ.አይ.ኤ እየሰራ ነዉ! እናንተ እንደምትሉት ሲ.አይ.ኤ ጠልቶናል  በእለቱ  የብሔራዊ መረጃውን ተነተርሳችሁ ያልዳሰሳችሁት ያልፈጠራችሁት የማላከክ ፖለቲካዊ ምህዳር የለም! ነገር ግን በዋነኛነት አንኳሩን ስህተት ዘንግታችሁታል!

በትክክል ለመረዳት ካላዳገታችሁ በስተቀር ህዝባችን ጀርባዉን እንዲሰጠን ያደረግነዉ እኛ እራሳችን መሆናችንን ንዉ  !

እኛዉ እራሳችን ነን ህዝባችንን ገፍትረን የሰደድነዉ!

እኛዉ እራሳችን ነን ተጠያቂዎቹ!

ከዚህ ወዲህ የምንሄደዉ የራሳችን መንገድ የለንም ቢኖርም በእናንተ ልቦና ዉስጥ የተቀበረዉ አካሄድ እርሱም የደም መንገድ ነዉ፤ ወደድንም ጠላን ማናችንም ከተጠያቂነት አናመልጥም ሁላችንም ፍርድ አለብን ይገባናል ።

ለምሳሌ ከኢትዮጵያ ዉጭ አንዳችንም በነጻነት መንቀሳቀስ ተስኖን ሳለ በሐገራችንም ዉስጥ ቀና ብለን እንዳንራመድ አንገት የደፋንበት ሁኔታ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤ በተቃራኒዉ ደግሞ በዉጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ሐይሎች በተልይም አሸባሪ ያልናቸዉ ድርጅት አመራሮች እጅግ ተከብረዉ እንዳሻቸዉ ሲመላለሱ በሐገር ዉስጥ የሚገኘዉ ህዝባችን ደግሞ እነርሱኑ አሻግሮ እየጠበቀ እንደሚገኝ ሁላችንም እናዉቃለን።

በመሆኑም ሳይመሽ ህዝቡም እራሱ ወደኛ ሳይመጣ እኛ እራሳችን ውደ ህዝቡ እንድሄድና የመጨረሻ እድላችንን እንድሞክር እያሳሰብኩ ከዚህ በታች ያሰፈርኩትን በስብሰባዉም ላይ የተሟገኩበትን ሁለት ፍሬ ነገር አቀርባለዉ።

  • በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ የሐገር ሽማግሌዎችን፣ የተባበሩት መንግስታት ልኡካኖችን፣ ተጽኖ ፈጣሪ ሐገራትን እና ከተለያየ አካል የተዉጣጡ ምሁራኖችን እንዲሁም የሐይማኖት አባቶችን ያሳተፈ ምክክሮችንበማድረግ የዉይይት መድረኮችን እናዘጋጅ።
  • የተመረጠና ብቁ የሆነ ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ይደረግ።
  • በበረሐ የሚገኙ ክተት ያወጁብንን የፖለቲካ ፓርቲዎች ባጠቃላይ ወደ ድርድር እንጥራና የሰላም በመፍጠር ብሔራዊ እርቅ እንቀመጥ።
  • በሐገር ዉስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋማት በዋነኛነት የቁጥር አንድና ሁለትን ህሳቤ እንዲያስፈጽሙ ተሳታፊ ይሁኑ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.