ዶክተር መረራ ጉዲናን እናሸልም ! (Bego Sew 2008 Award/ Ethiopia)

“እፅዋት በመኮትኮት ቅርፅ እንደሚይዙ ሁሉ፣ የሰው ልጅም በትምህርት ይበለፅጋል። ደካማ ሆነን እንደመወለዳችን፣ ጥንካሬ ያሻናል። ሁሉም በበቂ ሁኔታ የተሰጠን ሆነን ስላልተወለድን እርዳታ ያሻናል። […] ስንወለድ አብሮን ያልነበረና ያላገኘነው፣ በጉልምስና ዘመናችን ያገኘነው እያንዳንዱ ነገር የተገኘው በትምህርት ነው።” Jean Jaques Rousseau

ሰላም ለእናንተ የዚህ ገጽ ተከታታዮች፡፡ ስለ ዶክተር መረራ ጉዲና የማስተማር ዘዴና ክህሎት ከተማሪዎቻቸው የተለያዩ ፅሁፎች እየደረሱን ይገኛሉ። እነዚህን ፅሁፎች በተከታታይ ቀናቶች ውስጥ በገጻችን ላይ እየለጠፍን እንደምናስነብባቸሁ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ሌሎቻችንስ በእሳቸው የተማርን ምን እናስታውሳለን፣ የዶክተሩን ትውልድ የማነፅ አስተዋፅኦ እንዴት እናየዋለን? የሚሰማዎትን በመልዕክት መቀበያችን በኩል ያድርሱን፤ እኛም ለገጻችን ተከታታዮች እናጋራለን፡፡ በተጨማሪም ስማቸውን ለበጎ ሰው ሽልማት አስተባባሪ ኮሚቴ ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ከግንቦት 24 ጠዋት 12፡00 ሰዓት እስከ ሰኔ 24 ማታ 12፡00 ይስጡ፡፡ ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!

በስልክ፡ 0915445555
በቫይበር፡ 0915445555
በግንባር በመቅረብ፡ ለም ሆቴል ማትያስ ሕንጻ ቢሮ ቁ. 408
በፖስታ፡ 150035
በብሎግ፡ www.daneilkibret.com
በኢሜይል፡ begosew2008@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.