የውቕሮ ህዝብ በከፍተኛ የኤሌትሪክ ቃጠሎ በ10 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አደረሰ (አንዶም ገብረስላሴ)

ባለፈው ዓርብ 10 / 10 / 2008 ዓ/ም በውቕሮ ከተማ ዝናብ ለማሳለፍ ብለው በኣንድ ኮንቴይነር የተጠለሉትና ፖል ወድቆ ገመድ በመበጠሱ ያጋጠመ የኤሌክትሪክ ኣደጋ በ10 ሰዎች ላይ ያደረሰው የሞት አደጋ ለከተማዋ ነዋሪዎች ዘግናኝ ትእይንት ነበርና ክፉ ትውስታ ጥሎ ኣልፏል።

Electricበኣደጋው የሞቱት 9 ሰዎች ማንነት መለየት እስኪያቅት ድረስ በኤሌትሪክ ተቃጥለዋል። 10ኛው ተጎጂ፤ በተነፃፃሪ ብዙ የመቃጠል ኣደጋ አልደረሰበትም።

የኣደጋው ሰለባ የሆኑት ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኣደጋው ዘግናኝነት እንዳለ ሆኖ፤ ብዙዎችን ያስደነቀ ደግሞ ሌላ ተአምር ነበር፡፡ እናትዋ ጀርባ ላይ ታዝላ የነበረችው ህፃን ህይወትዋ በታምር ሊተርፍ ችሏል።

በኣደጋው የሞቱት ዜጎች ስም ዝርዝር ደርሶኛል።
፩) ወይዘሪት መዓርነት ገብረስላሴ ወረዳ ክልተኣውላዕሎ ቀበሌ ኣይናለም ኑዋሪ የነበረች
፪) ወይዘሪት ኣዝመራ ዘነበ ወረዳ ክልተኣውላዕሎ ቀበሌ ኣይናለም ኑዋሪ
፫) መለስ መብራህቱ ወረዳ ክልተኣውላዕሎ ቀበሌ ኣይናለም ኑዋሪ
፬) ገብረመድሂን ገብረስላሴ ወረዳ ክልተኣውላዕሎ ቀበሌ ነጋሽ ኑዋሪ
፭) ወይዘሪት ሰላም ገብረየሱስ ወረዳ ክልተኣውላዕሎ ቀበሌ ማይ ኲሓ ኑዋሪ
፮) ተማሪ ራህዋ ሓለፎም የወረዳ ክልተ ኣውላዕሎ ቀበሌ ጉለ ኑዋሪ
፯) ወይዘሮ ብሪ ገረዝሄር የውቕሮ ከተማ ኑዋሪ (በሂወት የተረፈችው ህፃን እናት)
፰) ወይዘሮ ለምለም ገብረሚካኤል የውቕሮ ከተማ ኑዋሪ
፱) ሃይላይ ገብረመድህን የውቕሮ ከተማ ኑዋሪ
፲) መስፍን ግርማይ የውቕሮ ከተማ ኑዋሪ የነበሩ ናቸው።
ይህ ዘግናኝ ክስተት የተፈጠረው በደርግ ግዜ የተተከሉና ያረጁ ምሶሶዎች በትንሽ ዝናብ ምክንያት ወድቀው የኤሌትሪክ ገመዱ በመበጠሱ ነው።

የውቕሮ ፖሎች 75 ዲግሪ ያጎነበሱና ለመውደቅ ትንሽ ምክንያት የሚፈልጉ ናቸው። በወርሃ ግንቦት ዘንቦ በነበረው መጠነኛ ዝናብ ምክንያት በሰው ህይወት ጉዳት ያላደረሰ ቃጠሎና 37 ፖሎች ወድቀው እንደነበር ይታወቃል።
በዚህም ምክንያት ኑዋሪው ባገኘው መድረክ ችግሩን ሲገልፅና ኣብዬቱታ ሲያቀርብ ነበር። በኣንድ ወር ውስጥ ብቻ ህዝቡ ዘጠኝ ግዜ ለ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና መብራት ሃይል ፅህፈት ቤት ኣብዬቱታ ኣቅርቦ ነበር። ዳሩ ሰሚ ኣላገኘም እንጂ።

በተመሳሳይ ክስተት በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኙ ኣይናለምና ብዓቲዓኾር ቀበሌዎች ስድስት ቆጣሪዎች ከኣቅማቸው በላይ እንዲሸፍኑ በማድረግ የኤሌክትሪክ ኣደጋ እንዲከሰት ሆኗል።

ከወር በፊት ባጋጠመው ኣደጋ ሁለት ኣዲስ ሙሽሮችን ጨምሮ 4 ሰዎች ሲሞቱ 30 ሰዎች ከባድ ኣደጋ ደርሶባቸው ህክምና አግኝተዋል።
በኣደጋው የሞቱት ወገኖች የቀብር ስነ ስርዓት ሲካሄድ በውቕሮ የሀዘን ታሪክ ከባዱ ነበር።
እናቶች ኣፈር ወደ ገላቸው በመነስነስ፣ ህዝቡ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ኣሰምቷል።
በኣይናለም ቀበሌ የሞቱት ሁለት ሴት ወጣቶች የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ህዝቡን እናረጋጋ በማለት ንግግር ለማድረግ የሞከሩት የምስራቃዊ ዞን የፕሮፓጋንዳ ሃላፊው ኣቶ ደሳለኝ ተፈራን የኣገር ሽማግሌዎች “ህዝቡ ሃዘኑን እንኳ ይግለፅበት እንጂ…! በኣሁኑ ሰዓት የናንተ ንግግር የሚሰማበት ትእግስት የለውም…! ” በማለት መልሷቸዋል።
በውቕሮ ከተማ ተመሳሳይ ንግግር ለማድረግ ሞክረው የተከለከሉ ሲሆኑ ትላልቅ ሰዎች ህዝቡ ምን ይላል ብለው ሲጠይቁ “ደርግ የተከላቸው ያረጁ የኤሌትሪክ ምሶሶዎችና ትራንስፎርሞሮች በየተራ እያቃጠሉ ሳይጨርሱን በኣስቸኳይ ነቅላቹ ኣውጡልን። እንደ ድሮ ኩራዛችን እንጠቀማለን…” በማለት ገልፆላቸዋል።

የውቕሮ ህዝብ በከፍተኛ የኤሌትሪክ ቃጠሎ ስጋት ውስጥ ይገኛል። ምክንያቱ 75 ዲግሪ ወደ መሬት የተጠጉና መውድቅያ ግዚያቸው የሚጠባበቁ ምሰሶዎች መቼ እንደሚወድቁ እርግጠኛ ኣይደለምና ነው።

የኤሌትሪክ ኣደጋ መንስኤዎች እየሆኑ ያሉ ያረጁ ትራንስፎርሞሮች፣ ያረጁና የበሰበሱ የኤሌትሪክ ምሶሶዎች(ፖሎች) ፣ ቆጣሪ ከኣቅም በላይ ቤቶች ማከፋፈል ሲሆኑ ለነዚህ ኣደጋዎች መባባስ ደግሞ የህዝብ ኣብዮቱታዎች ኣዳምጦ ኣስቸኳይ ጥገና ኣለማድረግ፣ ተገዝተው የሚመጡ እቃዎች በሙስና ምክንያት ጥራት መጉደል፣ የመንግስት ኣካላት ቸልተኝነትና የመብራት ሃይል ድርጅት ደንታ ቢስነት፤ የመብራት ሃይል ሰራተኞች የቅጥር ሂደት ከሞያ ብቃት ይልቅ የህወሓት ኣባል መሆንና የከፍተኛ ባለስልጣናት የኔትወርክ ተግባር ቅድምያ የሚሰጥ መሆኑ ዋነኞቹ ናቸው።
ከሁሉም የባሰ ደግሞ ችግሩ ተደጋግሞ መፍትሄ እንዲደረግለት የጠየቀው ህዝብ ምላሹ ዝምታ መሆኑ እጅግ ከማሳዘኑም በላይ እያወቀ እንዳጠፋ ይቆጠራል

በዚህ ዘግናኝ ኣደጋ፤ የሞቱት 10 ዜጎች፣ የቆሰሉት 8 ዜጎች፣ የተጎዳው የህዝብ ስነ ኣእምሮ ተጠያቂው ህወሓት መራሹ መንግስት ነው።
ስለዚ መንግስት ለሞቱትና ጉዳት ለደረሳቸው ቤተሰቦችና ካሳ መክፈል ኣለበት። ለተጎዳው የህዝብ ስነ ልቦና ደግሞ በይፋ ይርታ መጠየቅ ኣለበት።

መንግስት ኣስቸኳይ ይቅርታ ካልጠየቀ፣ ተገቢው ካሳ ካልከፈለ ሆን ብሎ እንደፈፀመው ተቆጥሮ ከህዝቡ ላንዴና ለመጨረሻ መለያየት እንደመረጠ ይቆጠራል።

* መንግስት ተጎጂዎች ካሳ ከፍሎ ህዝቡን ባስቸኳይ ይቅርታ መጠየቅ ኣለበት።

ለሞቱት ዜጎቻችን እግዝኣብሄር መንግስተ ሰማያት ያዋርሳቸው። ለቤተሰቦቻቸውና ክፉ ላየው የውቕሮ ህዝብ ፅናት እምኛለው።
ፎቶው ዛሬ ጥዋት በመቐለ 16 ቀበሌ የወደቀ የኤሌትሪክ ፖል ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.