ሌንጮ ባቲና ጌታቸው ረዳ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ሌንጮ ባቲና ጌታቸው ረዳ በአልጀዚራ ላይ ያደረጉትንን « ትንቅንቅ» አደመጥኩ።

oromo pጋሽ ሌንጮ “የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል ፥ ትንሽ ከፈት አድርጉልን ፥ እንድንገባ ይፈቀድልን ይላሉ ።” ጌች ያራዳ ልጅ ደሞ « ሌንጮ ሆይ ጫማሽ ላይ የኦነግ አፈር አለ እሱን ሳታራግፊ ሃገሬ አትገቢም ይላል» ።
ግራ የገባኝ ነገር ግን እሁን እይበለውና ወያኔ « የማሪያም መንገድ » ቢሰጣቸው እነ ሌንጮ ገብተው መንግስት ሊመሰርቱ ነው ማለት ነው ? « እንሆ በደጅህ ቆሜ አንኳኳለሁ የሚከፍትልኝም ባገኝ እገባለሁ አብሬም እራት እበላለሁ እሱም እንዲሁ ከኔ ጋ አብሮኝ እራት ይበላል » ነው ያለው መሲሁ! እንደ መጥሃፍ ቅዱስማ ቢሆን በር ማንኳኳት አሪፍ ነገር ነበር ። እነ ሌንጮ የአዝዕቅጥ አፋፋ ላይ የተሰራ በር አንኳኩተው የት ሊገቡ እንደሆነ አልገባንም ። ክፈቱልን ፥ አስፉልን ፥ ጥረጉልን ፥ ስሙን ፥ ጥያቄ ፥ ጥያቄ ፥ ጥያቄ ። ሃምሳ አመት በልመና እና በጥያቄ ፥ በጠባብነት እና በራዕይ አልባነት የተጓዙ መሪዎች ድሮም ቆሞ ከማንኳኳት የተሻለ ምንም ሊሰሪ አይችሉም ! ምድረ ደጅ ጠኚ! በነገራችን ላይ ሌንጭ ጊዜ ስላላገኘች እንጂ ፥ ከጌች ጋ እያወራች መሃል ላይ ስለ ሚኒሊክ ትዘበዝብ ነበር ። እድሜ ላአልጀዚራ!

ለማንኛውም በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ጌች « ትግሬ !» ስትባል ቱግ አለች ። “ሞቶ” ፐርሰንት « ትግሬ» ፥ ትግሬ ሃብታም ፥ ትግሬ የሃገር ደህንነት ፥ ትግሬ ጀነራል ፥ ትግሬ ፕሮፌሰር ሲሏት እንደ ሲላ የደስም ስሯ ከፍ ብሎ በቅንጧ ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር። የተባለው ስላልሆነ ሳይሆን ፥ ይህንን የሚሰማ ህዝብ ነገ ምን ሊያደርስ እንደሚችል ስለምታውቅ! ነብሴ ቱግ አልሽም ፥ ሰከንሽም ፥ ፈላሽም ፥ ደፈረስሽም እስከሚገባኝ ህዝቡ የጅሽን ከመስጠቱ አይመለስም ። የጊዜ ጉዳይ ነው ብዬሻለሁ ። ሰነፍ በልቡ “ጊዜ አይለወጥም ፥ ስልጣን ጉም አይደለም አይተንም ይላል ። ብልህ ግን ቀድሞ መጭ ይላል ። ስራሽ ያውጣሽ!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.