ሰበር ዜና…  ደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የስደተኛዉ ሲኖዶስ ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ዘረፋ አነጋጋሪ እየሆነ ነዉ

78def8ba-8df6-4ece-9871-ca5cb8f133c6

በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ የምትገኘዉ በኢትዮጵያዉ ሲኖዶስ የምትተዳደረዉ የኢትዮጵያ ኦርቶኦክስ ተዋህዶ መድሐኔያለም ቤተክርስቲያን በ28/06/2016 በትናንናዉ እለት ሲታመስ አመሸ።

በተዘዋዋሪ መንገድ የህወሃት መጠቀሚያ እንደሆነ የሚታወቀዉ የጆሐንስበርጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መድሐኒያለም ቤ/ክርስቲያን እጅግ አስገራሚ ክስተቶችና ስህተቶችን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን ትናንት ማምሻዉን የደቡብ አፍሪካ ኢሚግሬሽን ፖሊሶች ለቤተ ክርስቲያኗ መበጥበጥ ዋነኛ ተዋናይ ናቸዉ የሚባሉትን አባ ጾመ ልሳንን አስሮ ወደ ሐገር ቤት ለመመለስ ጥረት የተደረገ ሲኦን ጉዳዩ በምእመናኑ እና በሽማግሌዎች ስምምነት መሰረት ለ7 ቀናት ተራዝሟል።

የደቡብ አፍሪካ ኢሚግሬሽን ፖሊሶች የተካተቱበት ስምምነት እንደጠቆመዉ አባ ጾመ ልሳን ባጠቃላይ በእጃቸዉ ላይ የሚገኘዉን የቤ/ክርስቲያኗን መረጃዎች በቄስ አካሉ እማኝነት በደቡብ አፍሪካ ብሉም ፎንቴን ከተማ ላይ ለሚኖሩት ለቆሞስ አባ ገብረእግዛብሔር አስረክበዉ በ 7 ቀናት ዉስጥ ደቡብ አፍሪካን ለቀዉ እንዲወጡ የሚያዝ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኘዉ ሲኖዶስ በቅርቡ አባ ጾመ ልሳንን በመተካት አቡነ ያእቆብን ደቡብ አፍሪካ ላይ የሾማቸዉ ቢሆንም አቡነ ያእቆብ በበኩላቸዉ አባ ጾመ ልሳን ከዚያ ቤ/ክርስቲያን ላይ ካስልተወገደ ድረስ እግሬን አላነሳም በማለት አሻፈረኝ ብለዋል።

ለሁለት ተከፍሎ በመበጣበጥ ላይ የሚገኘዉ ይህዉ የቤ/ክርስቲያኗ ጉዳይ ወደ ሚስጥር መወጣጣት በመሸጋገሩ ባሳለፍናቸዉ ጥቂት አመታቶች ብቻ 422 ግለሰቦች በወያኔ ባለስልጥናት አማካኝነትና በዚህችዉ ቤ/ክርስቲያን የጉብኝትና የግብዣ ደብዳቤ ወይም ( Invitation later ) በመጠቀም ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር መካሄዱን የሚያጋልጡ ሰነዶች ኢትዮጵያ ከሚገኘዉ የደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ የተገኘ ሲሆን በልላ በኩል ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ እንደተዘገበዉ በስደተኛዉ ሲኖዶስ የምትተዳደርዉ በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ ላይ የምትገኘዉ ቅድስት ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ላይ በ2011 የተፈጸመዉን የዘረፋ ወንጀል በሚያረጋግጥ መልኩ በቂ የድምጽና የምስል መረጃዎች ከዚሁ አካባቢ አፈትልኮ ወጥተዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ መረጃ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸዉ አካላቶች በተለይም የስላሴ የዘራፋ ጉዳይ የሚመለከታቸዉ ግለሰቦች ቤ/ክርስቲያኗ በተለይም በዘረፋዉ ወቅት በቀጥታ ተጎጂ የነበሩት አባ ሳሙኤል ክስ ለመመስረት ባለመፈለጋቸዉ እና ለፈጣሪ በመስጠታቸዉ አንመለስበትም ያሉ ቢሆንም አስፈላጊ በሆነበት ወቅትና ሰአት ግን መረጃዎቹ ባጠቃላይ ጥቅም ላይ እንደሚዉሉ ተናግረዋል።

ዜና በልኡል አለም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.