ታዛዥና እስረኞችን የሚያጉላላ ዳኛ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ተሾሟል

13620392_10209593637788529_3481941482671804827_n የምታዩት ግለሰብ ዳኛ ዳኜ መላኩ ይባላል። ሃብታሙ እንዳይታከም እገዳ ያደረገ፣ በቀጠሮ ላይ ቀጠሮ እየሰጠ በ እስረኞች ላይ ትልቅ መጉላላትን የፈጠረ፣ ቀጠሮ ሰጥቶ ብዙ ጊዜ የሚቀር ዳኛ ነው።

“ከሰብዓዊነት በታች ወድቃችሁ ሁላችንንም ክፉኛ አሳዘናችሁን!አምናለሁ፣ ሀብትሽ ላይ የተቃጣውን የክፋት መንፈስ የፍቅር አምላክ ይመክተዋል!” ይላል ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ የዛሬውን አሳዛኝ የፍርድ ቤት ድራማ ተመልክቶ።

ዳኛው ዳኜ መላኩ ይባላል። ላለፉር አንድ አመት በቆጠሮ ላይ ቆጠሮ እየሰጠ እነ ሃብታሙን ሲያከራትትና ሲያጉላላ የነበረ ዳኛ ነው። ይህ ዳኛ የሕወሃትን መመሪያ እየተቀበለ የሚሰራ ዳኛ ተብዬ ካድሬ በመሆኑ በቅርቡ እንደውም ትልቅ ሹመት አግኝቷል። ዳዊት ሰለሞን በዚህ ዳኛ ዙሪያ የሚከተለውን ጽፏል፡

“የሐብታሙ አያሌው የጤንነት ጉዳይ አሳሳቢ በመሆኑና ከአገር ውጪ የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ የጉዞ እግዱ እንዲነሳለት ለቀረበ አቤታቱ ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም የመሐል ዳኛው ዳኜ መላኩ ባለመምጣታቸው የሐብታሙ፡ጉዳይ ለሐሙስ ተቀጥሯል ። በችሎት ያልተገኙት ዳኛ ዳኜ መላኩ በቅርቡ በኢህአዴግ ፓርላማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት በመሆን መሾማቸው አይዘነጋም ።ዳኜ ለረዥም አመታት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዳኝነት ከመስራታቸው በላይ የህሊና እስረኞችን ጉዳይ በመከታተል የስርዓቱን ውሳኔ በፍርድ ቤት ስም ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ለፕሬዘዳንትነት አብቅቷቸዋል ። ሰውዬው ልጆች ፣ሚስት ፣ቤተሰብና ህሊና ካለውም በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን የህፃን አባትና ፍትህ ፍለጋ ችሎት ውስጥ ራሷን ስታ፡በወደቀችው ባለቤቱ ስም እንጠይቃለን ።”

Comments are closed.